የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ አዲስ አበባ ገቡ
*********************
የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡