የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ
************************
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ፕሬዚዳንቱ “ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ትግል መስዕዋት ለከፈሉ ጀግኞች መታሰቢያ ሀውልት ስር አበባ አስቀምጠዋል”ብለዋል፡፡
የዓድዋ ድል መታሰቢያን የጎበኙት ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ ባሳየችው ፈጣን ለውጥ አድናቆታቸውን መግለጻቸውንም አመላክተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አመሻሽ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዚዳንቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲሁም በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡