ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በኢንቨስትመንት፣ ባሕል እና ትምህርት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ
**************************
ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በኢንቨስትመንት፣ ባሕል እና ትምህርት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሰፊ መጠነ ርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፕሬዝዳንቱ በቅርቡ በታደሰው ብሔራዊ ቤተመንግሥት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፈረንሳይ ለብዙ ዘመናት ተዘንግቶ ለቆየው የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ላደረገችው የእድሳት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ቤተመንግሥቱን ተዘዋውረው የጎበኙት ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው አስደማሚውን የቤተመንግሥት እድሳት አድንቀው ፤ በዓድዋ መታሰቢያ ግንባታ እንደታየው የኢትዮጵያን ታሪክ እና ባሕል ለማክበር ለተደረገው ጥረት ክብር ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በተመለከተም ረጅም ዘመን ለቆየው መሻት ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት ሁለቱ ወገኖች በጋራ ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የነበራቸውን ውሎ እና የጋራ ፍላጎታቸውን የትብብር ቁልፍ ጉዳዮች የተመለከተ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡