ጅቡቲ ወደብ የደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ወደ ኢትዮጵያ እየተጓጓዘ ነው
************
ዩሪያ እና ዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ 6 መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተገልጿል።
እስከአሁን በወደቡ ከደረሰው 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ 256 ሺህ 398.2 ሜትሪክ ቶን የሚሆነው ወደ ኢትዮጵያ መላኩን በኢትዮጵያ የጅቡቲ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
ቀሪው ማዳበሪያ በመጓጓዝ ላይ እንደሚገኝም በመረጃው ተያይዞ ተገልጿል።
በተጨማሪም 56 ሺህ 000 ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች ሰባተኛ መርከብ ትናንት ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ደርሳ ጭነት እያራገፈች እንደምትገኝ ተጠቁሟል።
በሚቀጥሉት ቀናትም ተጨማሪ 4 የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።