ባለፉት 6 ዓመታት መንግስት ሁሉን አቀፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው፡- ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)
*******************
ባለፉት 6 ዓመታት መንግስት ሁሉን አቀፍ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው ሲሉ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም አዘጋጅነት በሚቀርበው ‘ኢትዮጵያ ኢን ፎከስ’ ፕሮግራም ላይ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚያዊ፣ በማበራዊና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል።
ባለፉት ዓመታት መንግስት በወሰዳቸው እርምጃዎችም በሁሉም መስኮች አካታችና አሳታፊ ዕድገት በማስመዝገብ ማህበራዊ አካታችነትን ማረጋገጥ መቻሉን ሚኒስትሯ በማብራሪያቸው ገልጸዋል።
በዚህም መንግስት በቀየሳቸው የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎች ተጨባጭ ለውጥ መመዝገባቸውን ነው ያስረዱት።
ለአብነትም በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበና አካታች በሆነ መልኩ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን አንስተው፣ በዚህም ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል።https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0ya4UxdnD3SqqtMaUEJKeBgoUQy2Wy8Vf2ubEmBMFrrWyZExWnECFKBFuxEG8Z77ml