የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው
*****************
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 17ኛ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ የ16ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔን ያጸደቀ ሲሆን አሁን ላይ አጠቃላይ የትምህርት ረቂቅ አዋጅ ላይ የቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ እያዳመጠ ይገኛል፡፡
የረቂቅ አዋጁን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በምክር ቤቱ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር ) ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ እያቀረቡ መሆኑን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ምክር ቤቱ በቀጣይም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ሹመትን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡