የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓልን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ
***************
85ኛውን የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል አስመልክቶ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ከአዊ ብሄረስብ አስተዳደር ጋር በመተባባር ያዘጋጀው ሲምፖዚየም መካሄድ ጀምሯል።
በሲምፖዚየሙ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዊ ብሄረስብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይተነው ታዴ፤ እንኳን ለ85ኛው ታሪካዊውና አንጋፋው የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ክብረ በዓሉን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ አቶ አይተነው ገልፀዋል።
የአገው ፈረሰኞች ማህበር ለረጅም አመታት ሲጠይቅ የነበረው በእንጅባራ ከተማ ለገቢ ማስገኛ ቦታ 2 ሺህ 860 ካሬ ሜትር ቦታ መፈቀዱንም መናገራቸውን ከአስተዳደሩ ከሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።