አሜሪካ ለኤች አይ ቪ ቫይረስ ህክምና የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ገለፀች
********************
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር ለሚኖሩና በቫይረሱ ምክንያት ችግር ላይ ለሚገኙ አካላት ህክምናና ድጋፍ እንዲያገኙ አሜሪካ የምትሰጠውን ድጋፍ እንደምትቀጥል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትረ ስልጣናቸውን በተቀበሉበት ቀን ካስተላለፏቸው ትእዛዞች መካከል አሜሪካ የምትሰጠው ማንኛውም የውጭ እርዳታ ለሚቀጥሉት 3 ወራት እንዲቆም መወሰናቸው ይታወሳል፡፡
በተለይም ለዓለም ጤና ድርጅት 18 በመቶ የገንዘብ ምንጭ የሆነችው አሜሪካ በ12 ወራት ውስጥ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት ለመውጣት መወሰኗ ድርጅቱ “ጤና ለሁሉም” በሚል እየሰራቸው ለሚገኙ ስራዎች ከፍተኛ የፋይናንስ ችግር እንደሚገጥመው ሲገለፅ ቆይቷል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ይፋ ባደረጉት መረጃ ሃገሪቱ በ55 ሀገራት ከኤች አይ ቪ ቫይረስ ጋር ለሚኖሩ ወገኖች እየሰጠች የነበረውን አስቸኳይ ድጋፍ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
ለህይወት አድን መድሃኒት መግዣ፤ ለህክምና፣ ለምግብና መጠለያ እንዲሁም በስራው ላይ ለሚገኙ የአስተዳደር ወጪዎች የአሜሪካ ድጋፍ ይቀጥላል ነው የተባለው፡፡
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0awFXVBndBvptzSaw7E7hhi3AXRwcZEGfXKN6PvKMPs1MfQ13xvhwjkr2mFxhnKaNl