በዘመናዊ መንገድ እንጆሪ እና ሳፍሮን ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ኩባንያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው
*******************
በ2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስትመንት በዘመናዊ መንገድ እንጆሪ እና ሳፍሮን በማምረት ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ኩባንያ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ ወደ ስራ ሊገባ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ የተሰኘው ኩባንያው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና የአፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናሱር ማሃማት ተፈራርመዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) ኩባንያው ይዞት የመጣው ፕሮፖዛል በኮርፖሬሽኑ የስራ ሂደት ውስጥ አዲስ መሆኑን ጠቅሰው ለውጤታማነቱ ተገቢው ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ናሱር ማሃማት በበኩላቸው ኩባንያው ኢትዮጵያን ግንባር ቀደም የእንጆሪ እና ሳፍሮን ላኪ ሃገር ለማድረግ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡
አፍሪካን ፋርሚንግ ኢንዱስትሪስ ኩባንያ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ሺህ ካሬ ሜትር የለማ መሬት እና 3 ሺህ ካሬ ሜትር ሼድ ተረክቦ ወደ ስራ እንደሚገባም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡