TGStat
TGStat
Qidiruv uchun matnni kiriting
Ilg‘or kanal qidiruvi
  • flag Uzbek
    Sayt tili
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Saytga kirish
  • Katalog
    Kanal va guruhlar katalogi Kanallar qidiruvi
    Kanal/guruh qo‘shish
  • Reytinglar
    Kanallar reytingi Guruhlar reytingi Postlar reytingi
    Brendlar va shaxslar reytingi
  • Analitika
  • Postlarda qidiruv
  • Telegram'ni kuzatish
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

17 May, 23:57

Telegram'da ochish Ulashish Shikoyat qilish

ኢትዮጵያ እየፈጠረች ያለው የቴክኖሎጂ አቅም የታየበት መድረከ
**************

በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ የሆነው እና በዓይነቱ ልዩ የሆነው ETEX2025 ኢትዮጵያ እየፈጠረችው ያለው አቅም ምን ያክል እንደሆነ ያሳየ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ETEX2025 ላይ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡት ስታርታፖች ከሌላው ዓለም ከመጡት አቻዎቻቸው እና ከኢንቨስተሮች ጋር ትስስር ሊፈጥሩ መቻላቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም ላይ እንደሀገር የነበሩ ስታርታፖች በጣም ጥቂቶች እንደነበሩ ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በአሁኑ ጊዜ ከሁለት ሺህ በላይ ስታርታፖች እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ መካከል ምርቶችን እና አገለግሎቶችን ማቅረብ የጀመሩ እና ከፍተኛ ተስፋ የሚጣልባቸው መኖራቸውን አውስተው፣ በዚህ ኤክስፖ ላይ አገልግሎቶቻቸውን እና ምርቶቻቸውን ያቀረቡት በልዩ ሁኔታ የተመረጡ እንደሆኑ ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ ካላት ከፍተኛ የሰው ቁጥር ውስጥ 70 በመቶ እና ከዚያ በላይ ወጣት እንደሆነ የጠቀሱት ዶክተር ባይሳ፣ ስታርታፕ ይህን የወጣት ኃይል አምራች እንዲሆን እና ለሀገር ጠቃሚ ሥራ እንዲሠራ ያስችለዋል ብለዋል፡፡

መንግሥት የሀገርን ብልፅግና ለማረጋገጥ ባለው ቁርጠኝነት ስታርታአፕ ላይ አተኩሮ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወጣቶች ብቁ የኢንዱስትሪ ፈጣሪ እንዲሆኑ አቅማቸውን የማጎልበት እና የሥራ ካባቢን የማመቻቸት ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ዘርፍ እንደ ሀገር ያሉብንን ችግሮች መፍቻ፣ ልማትን ማፍጠኛ እና ተወዳዳሪነትን ማረጋገጫ እንዲሆን መንግሥት በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ያሉት ሚኒስትር ዴታው፣ በፈጠራ የሚመራ ኢኮኖሚን ማጎልበት ደግሞ ዓላማው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን በማፋጠን ውጤታማ የሆኑ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ስታርታፖች ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ነው ዶክተር ባይሳ የተናገሩት፡፡

ስታርታፕ ለበርካታ ሀገራት የፈጠራ መስክ እና የዕድገት መነሻቸው እንደሆነ የጠቀሱት ዶክተር ባይሳ፣ ኢትዮጵያም የምትፈልገውን በፈጠራ የታገዘ ኢኮኖሚን ለመገንባት ለስታርታፖች ከሀሳብ ጀምሮ በየደረጃው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁ የሆነው እና በዓይነቱ ልዩ የሆነው ETEX2025 ኢትዮጵያ እየፈጠረችው ያለው አቅም ምን ያክል እንደሆነ ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው፣ ቀጣይ ተስፋችንንም ያመላከተ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በለሚ ታደሰ

6.6k 0 3 23
Katalog
Kanal va guruhlar katalogi Kanallar to‘plamlari Kanallar qidiruvi Kanal/guruh qo‘shish
Reytinglar
Telegram-kanallar reytingi Telegram-guruhlar reytingi Postlar reytingi Brendlar va shaxslar reytingi
API
Statistika API'si Postlar qidiruvi API'si API Callback
Kanallarimiz
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
O‘qish
Blogimiz Telegram tadqiqoti 2019 Telegram tadqiqoti 2021 Telegram tadqiqoti 2023
Kontaktlar
Справочный центр Qo‘llab-quvvatlash Email Vakansiyalar
Har xil narsalar
Foydalanuvchi shartnomasi Maxfiylik siyosati Ommaviy oferta
Botlarimiz
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot