ሃማስ 9 ተጨማሪ የእስራኤል ታጋቾችን ለመልቀቅ ሀሳብ አቀረበ
*************************
በእስራኤል እና ሃማስ መካከል እየተካሄደ ባለው ድርድር፤ ሃማስ 9 ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ሀሳብ አቅርቧል።
ድርድሩ መደረግ የጀመረው የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ላይ አዲስ ጥቃት ከከፈተ ከሰዓታት በኋላ ነው።
ሃማስ ዘጠኝ ታጋቾችን ለመልቀቅ የተስማማ ሲሆን፤ በምላሹ የ60 ቀናት ተኩስ አቁም እና እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን እንድትለቅ መጠየቁን አንድ የፍልስጤም ባለስልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ባለሥልጣኑ አክለውም ስምምነቱ ከተደረገ በቀን 400 የእርዳታ መኪኖች ወደ ጋዛ እንዲገቡ እና ህሙማንን ከጋዛ እንዲለቁ ያስችላል ብለዋል።
እስራኤል በበኩሏ ቀሪዎቹ ታጋቾች በህይወት ስለመኖራቸው ማረጋገጫ እና ዝርዝር መረጃ ጠይቃለች።
አዲሱ የተኩስ አቁም ድርድር በኳታር እና በአሜሪካ ሸምጋዮች በዶሃ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እየተካሄደ ነው።
ኢቢሲ የፌስቡክ ገፅ
ኢቢሲ ድረ ገፅ
ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ