👉ከተከታታያችን ቤተሰብ የተላከ ጥያቄ፦
«አንድ ተቋራጭ በመጀመሪያው ዉል (ጨረታ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ) Rebate ቢኖረው እና በዋጋ ንረት ምክንያት የዋጋ ማሻሸያ ቢሰራለት፤ አዲሱ ውል/ የተሻሻለው ውል REBATE ይደረጋል ወይስ አይደረግም?»
🏷አንድ የሥራ ተቋራጭ በመጀመሪያው ውል መጀመሪያ ላይ የዋጋ ቅናሽ አቅርቦ ጨረታውን ቢያሸንፍ እና በኋላ ላይ የዋጋ ማስተካከያ (price adjustment) ከተደረገ በዋጋ ንረት ምክንያት የተሻሻለው ውል ባህሪ በአብዛኛው የሚመሰረተው በውሉ ላይ በተመለከተው «የዋጋ ማስተካከያን በሚመለከት በተቀመጡ ስምምነቶች (terms of price adjustment» ላይ ነው።
ለምሳሌ የግንባታ ሥራው የሕንጻ ግንባታ ከሆነ በሀገሪቱ Public Procurement Agency (PPA) General Condition of Contract, Clause 62 ሥር ባለው ዝርዝር መሰረት የሚዳኝ ይሆናል።
ይህንን በሚመለከት ተዋዋዮች በልዩ ድንጋጌ (Special Conditions) ያስቀመጡት ስምምነት ካለ ገዢ ሆኖ ይቆጠራል።
💫ነገር ግን የተለመዱ አሠራሮችን እንደመነሻ ለማንየት ከፈለጉ፦
1ኛ) በዋጋ ማስተካከያው (adjustment) የተጠየቀበት ምክንያት የዋጋ ንረትን ወይም የግንባታ ቁሳቁስ (Material Cost) ወይም የሰራተኛ ወጭ (Manpower cost) ወይም የማሺነሪና እቃዎች (Machineries anr tools cost) ለውጦችን ከግምት ውስጥ ያስገባ ሆኖ የተሰላ ከሆነ ይህ በአጠቃላይ የውል ዋጋ እንደጨመረ ይቆጠራል እንጂ የዋጋ ቅናሽ አይደለም።
ተቋራጩ በዋጋ ንረት ምክንያት የጨመረውን ወጪ እንዲያስተላልፍ ሊፈቀድለት ይችላል፣ ይህም በመጀመሪያ ከተስማማበት ዋጋ በላይ ይሆናል።
2ኛ) የዋጋ ቅናሽ የሚለው ጽንሰሀሳብ በውል ትርጉም መሰረት ተጫራቹ በውድድር ሰዓት ያስገባው ዋጋ አሸናፊ እንዲያደርገው የሚያስገባው በጊዜው የሚተገበር የጠቅላላ ዋጋን (--%) የቅናሽ እድል እንጂ በየጊዜው ተግባራዊ እንዲደረግ የፈቀደው አይደለም።
በኋላ ላይ የመጣው የዋጋ ማስተካከያ ተቀናሽን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ሆኖ ሊሰላ ይችላል።
ይህም ማለት አዲስ የተሰራው ዋጋ የመጀመሪያውን የዋጋ ተቀናሽ (Rebate) ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የተተከለ ዋጋ ሊሆን ይችላል።
3) አንድ ጊዜ አሸናፊ ሆኖ የተዋዋለ ተጫራች በኋላ ለሚመጣው የዋጋ ማሻሻያ ላይ ለሚገባው ውል “ቅናሽ የተደረገ” ተብሎ ሊቆጠር የሚችለበት አግባብ የለም።
ምክንያቱም ቅናሹ በመጀመሪያ ስምምነት ላይ በተደረገው ዋጋ ላይ ነው አዲሱ ዋጋ (ከዋጋ ግሽበት በኋላ) ከመጀመሪያው ጨረታ የበለጠ ወጪን የሚያንፀባርቅ ሊሆን ይችላል እንጂ ተቀናሽን ታሳቢ ማድረጉ ምንም አይነት ጥቅም የለውም።
ስለሆነም ቀድሞ የነበረው (ዋናው) ተቀናሽ በዋጋ ግሽበት ምክንያት ተስተካክሎ ይቀራል ማለት ነው።
⭐️Youtube ገፃችን ላይም ቤተሰብ ይሁኑ👇
https://youtube.com/@ethiopianconstruction?si=i3B2u9LyWBNjqAAO
@etconp