👉በካዛንቺስ 13 ሺህ 752 መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው ተባለ!
በካዛንቺስ በ18 ወራት ተገንብተው የሚጠናቀቁ 13 ሺህ 752 የመኖሪያ ቤቶች በመንግስትና በግል አጋርነት ሊገነቡ ነው።
መኖሪያ ቤቶቹ ከአያት አክሲዮን ማህበር ጋር በትብብር የሚገነባ "የካሳንቺስ አያት መኖሪያ መንደር" መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል አጋርነት የሚስራ መኖሪያ ቤቶች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፤ መኖሪያ ቤት አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።ይህንን ለመመለስ የህግ ማሻሻያ ተደርጓል።በዚህም ቤቶችን ለመገንባት በአራት አማራጮች በመንግስት፣ በመንግስትና በግል፣ በማህበርና በሪል ስቴት በርካታ ቤቶች እንዲገነቡ ማድረግ ነው ብለዋል።
በእነዚህ አማራጮች እስከ አሁን 270 ሺህ ቤቾች መገንባታቸውን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች፤ የቤት አቅርቦት በማስፋት አብዛኛውን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
የአያት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዐቢይ ማሞ፤ "የካሳንቺስ አያት መኖሪያ መንደር" 13 ሺህ 752 የመኖሪያ ቤቶች በውስጡ እንዳሉት ገልፀዋል።መኖረያ ቤቶች፣ ንግድ ማዕከላት፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ፕላዛዎች፣ የልጆች መጫወቻና የስፖርት ማዘውተርያዎችን፣ መዋለ ህጻናቶች፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችን፣ የመኪና ቻርጂንግ እስቴሽኖች፣ የመኪና እና የብስክሌት ፓርኪንግን አካቶ በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት የሚገነባ ይሆናል ብለዋል።
Via EPA
@etconp