👉የሲሚንቶ ግብይት ላይ በተወሰደ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ ዋጋው በግማሽ ቀንሷል – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)
🚧የሲሚንቶ ግብይት ላይ በተወሰደ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ የተረጋጋ አቅርቦትና ግብይት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ዋጋው በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የፌደራልና የክልሎች የንግድ ዘርፍ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ዛሬ አካሂደናል ብለዋል፡፡
በ6 ወራት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሚሊየን 50 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
ከጠቅላላው ሀገራዊ የወጪ ንግድ 3 ነጥብ 28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን ገልጸው፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር 1 ነጥብ 71 ቢሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል።
የቅዳሜና እሁድ ግብይት ማዕከላትን 1 ሺህ 213 ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል።
የሲሚንቶ ግብይት ላይ በተወሰደ የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ የተረጋጋ አቅርቦትና ግብይት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር ዋጋው በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡
በስድስት ወሩ ዓለም አቀፍ ጥራቱን የጠበቀ የጥራት መንደር በ7 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው÷ በተቋሙ ቅጥር ግቢ 730 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ የወጪ ንግድ ማሳያ ማዕከል ተገንብቶ የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅሞችን በማስተዋወቅ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የንግድ ትስስርን በማጠናከር አስተማማኝ የገበያ እድል ከመፍጠር አንጻር የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግም እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
Via FBC
@etconp