በዮኒቨርሲቲ ቆይታችሁ እነዚህ ነገሮች ብታረጉ ጥሩ ነው ❗️
💡....ዲያሪ መፃፍ .....
🎓 የካንፓስ ቆይታ በጣም የሚገርሙ moment ያሉበት ነው ።በቃ 3 or 5 የደስታ ዘመናት ... የሚገራርም ሰው ታያላችሁ ....የሚወዛገብ ፤ የሚወሳሰብ የሚፈላሰፍ ፤ ምንም ዲጭ የማይልበት ፤ ተንከሲሲስ ፤ በጣም ጅል ፤ አራዳ ነኝ ባይ ገገማ ....ኧረ ምኑ ቅጡ ....በህይወታችን አዳዲስ ነገሮች ይከሰታሉ ። ነገር ግን እንረሳቸዋለን ቶሎ ቶሎ አዳዲስ ነገር ስለሚፈጠሩ ይረሳል ። እናንተ ደግሞ ከፈለጋችሁ መፃፍ ብታረጉት ፤ ወደፊት ፊልም የመስራት ዕቅድ ካላችሁ ሚገራርሙ ገፀባህራያት ታገኛላቹሁ....ብቻ በላይፋቹ የማታገኙት ዕድል ስለሆነ በርትታቹሁ?...አዳዲስ ነገር ሲኖር በወረቀት (ዲያሪ) "ወይም ስልካቹም ላይ ቢሆን አስፍሩት ..! ትዝታዎቻቹ ናቸው እንዳትረሱት...ሙድ የተያዘባችሁ ሙድ የያዛችሁትን ...የሚያስቅ ፤ የሚያሳዝን፤ የሚያናድድ ብቻ ....ቸክችኩ ቢያንስ ልጆቻችሁ ትሰጧቹሃላቹ እነሱም ካምፓስ ሊገቡ ሲሉ ....በየቀኑ ሳይሆን የሆነ ነገር ሲፈጠር ፃፉት ...አሁን ምንም ላይመስላቹሁ ይችላል ግን አልፎ ስታዩት የምርም ትደሰታላቹሁ .....
💡አዲስ ቋንቋ መማር ......❗️
📚 ዶርም የምትሰባሰቡት ከየአቅጣጫው ነው ። ብዙ የማታውቁትን የሚያቁ ይሄም አለ❓... ያምሃል...! የሚያስብሉ ዕውቀቶች ታገኛላችሁ ። አንዱ ደሞ ቋንቋ ነው ። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያለ ተናጋሪ ያላቸው እንደ ኦሮሚኛ ፣ሲዳመኛ ፣ትግረኛ፣ ሱማሌኛ ቋንቋዎች የሚችሉ ልጆች ዶርም ካገኛችሁ በቀን 5 ቃልም ቢሆን ቀስ እያላችሁ ተማሩ .....የምር ይጠቅማቹሃል ። ቋንቋ መልመድ ጥሩ ነው ። ሁላቹም ጋር አዲስ ቋንቋ ከሌለ ደሞ ጓደኞቻችሁን የምታስታውሱበት አለ ኣ በቃ ....አዲስ የባህርማዶ አንድ ቋንቋ በጋራ ተለማመዱ ...ስፓንሽ ወይ ደሞ ፈረንች ...የተመቻችሁ በጋራ በቀን ትንሽ ነገር አጥኑ ። የ3 or 5 አመት ጓደኞቻችሁን ስትለዮዎቸው ማስታወሻ ይሆናቹሃል ። ፈታ እያላችሁ ጠዋት ላይ 5 ቃላት ምናምን ሸምድዱ የምርም ጓደኝነታችሁ ለማጠንከር ያግዛቹሃል ።
💡መክሊታችሁን ማዳበር ......!
📚 የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተለያዩ መክሊቶች ተሰጥቶታል ። ታዲያ እናንተም የተፈጥሮ ስጦታችሁን በክበብ በመሳተፍ ማሳደግ አለባቹሁ፣ በገገሙ ትምህርት ብቻ ካንሰር ነው የሚሆንባቹሁ ...ትወና የምትሞክሩ....ግጥም መጣጥፍ የምትሞክሩ ....ስዕል ....ሃይማኖታዊ ነገሮች የምትሞክሩ ብቻ ግቢ ላይ ብዙ ክበቦች አሉ ...የሴቶች ...የበጎአድራጎት ...የሌለ የለም ....እና ተሳተፉ ማህበር አለ ...ዕቁብ፣ ዕድር ሁላ አለ (ቀልዴ ነው ...) ....በቃ በዓል ግዜ ደስ ይላል ። የምትወዱት ከኖርማል ትምህርታቹ ላይ የሚደበል ...ዘፈን ከሆነ ...ስፓርት ከሆነ ...ኳስ ከሆነ .....ብቻ የምትወዱትን አንድ ነገር አዳብሯቹሁ ። ተገኙ .....በገገሙ ትምሮ ብቻ አይነፋም ...!
💡 የተለያዮ EVENT እና TOUR እንዳትቀሩ ...
በግቢ ቆይታ ፍራንክ ባይኖራቹ ራሱ ተበዳድራቹ ሀገር መጎብኘት አሪፍ ነው ። በቃ ceremony ሲኖር ....ይሂዱ ባክህ አትበሉ ዳግም የሚገኝ ነገር አይደለም ጦቢያን የምር የምታውቁበት ነው ። ትምህርተ ጋር ካልተጋጨ በየ ግዜው በአስተባሪዎች ጉዞ ይኖራል ። ስለዚህ.... አትቅሩ ...የመፅሀፍ ምረቃዎች ....አነቃቂ ንግሮች ...ትያአታራዊ ዝግጅቶች ይደረጋሉ .....አትቅሩ ....ታዋቂ ሰዎች በየግቢ እየመጡ በተለይ ወጣቶች የህይወት ልምዶቻቸውን ስለሚያጋሩ .....የምታደንቋቸው ሰዎች በየትኛው መንገድ ነው የተሳካላቸው ....የሚለው የህይወት ጉዞን ትማሩበታላቹሁ ...የፈታ ኢቨንቶችም አሉ በቃ ....ፈተና ሲያልቅ ምናምን ከች የሚሉ እና ሳትንዘላዘሉ ተሳተፉ ....እነ ሮፍናን ደግሰው መቼስ አይቀርም .....እነ እሸቱ መለሰ እየቀለዱ መቅረት ይከብዳል ....
⏰️ አዳዲስ ነገሮች ሞክሩ ...አትፍሩ ❓
📚 አዳዲስ ነገሮች የማድረግ ዕድሉ ስለሚኖረን ምንአቧቱ በእናት ሆድ አይለመድ አትፍሩ ሞክሩ ....ታዲያ ሱስ ምናምን ሳይሆን አሪፍ የሚባሉ ነገሮች የፍቅር ህይወትም ቢሆን ትምህርትን በማይነካ መልኩ ቢደረግ አይከፋም (ታዲያ ለሴሚስተር የሚቆይ ሳይሆን የምር መሆኑኑን ካመናችሁ ..) ....በግ ተራም ቢሆን አንዳንዴ መሄዱ ለክፉ አይሰጥም (አመራችሁ ዴ ቀልዴ ነው..) .....ሀገራቹ ሄዳቹሁ ለማውራትም ኮ መሞከሩ አይከፋም ።ግን ብዙ አትንዘላዘሉ ...ቸክሉ ...በቃ የሚያስደስታችሁን አዲስ ነገር ሞክሩ .....ብዙዎች ካንፓስ ሃይማኖተኛ ያረጋቸዋል አንዳንዶች ደሞ ...."ፈላስፈ አንዳነዶች ....ዘልዛላም ይሆናል ....አንዳንዴ ሳታስቡት ሃርድ ውስጥ ትገቡ ይሆናል ....ታዲያ ያን ግዜ አትጨናነቁ ...Normal ነው ። በተረፈ መልካም ካንፓስ!
💬በመጨረሻም ካንፓስ ላይ ቆይታቹሁ ልትደሰቱበት የሚችሉበትን የማትፀፀቱበትን ነገር ብቻ ከውኑ ። በቃ ያማረ የግቢ ቆይታ እንዲሆንላቹ ምኞቴ ነው ። ጥሩ ጥሩ ነገሮች ሊያውም የማይደገሙ ሲያጋጥማቹሁ አትለፉ እርግጥ ዋናው ጉዳያቹሁ ትምህርት ቢሆንም ...መደሰቱ መሳተፉ አይከፋም ። አይዞን በቆንጆ ሁኔታ ይታለፋል ።