የየሻረግን ቀልብ እና ፈገግታ ስለምን ነው የኖርኩት...!
የሻረግ የቤት ሰራተኛችን ነበረች ደግ ነች፤ ባለሙያ ናት፡ ዝምተኛ ነች ፤ ታዛዥ ነች ።
እናቴ አርፋ አመት እንደሞላት አባቴ የሻረግን አገባት ። የሰፈሩ ሰው ሁሉ አባቴን እና የሻረግን ወቀሳቸው ። እኔ በሂደት ነው የየሻረግ ሚና እና ቦታ እንደ ተቀየረ የገባኝ ።
የሻረግ እኔን ማዘዝ ስትጀምር ፣ ስትቆጣኝ ፣ ተጨማለቅክ ስትለኝ ፣ ትህትናዋ ፣ ደግነቷ ሲሰወርብኝ ፤ አባቴ ጋ መቃለድ ስትጀምር ፣ የልጅ አዕምሮዬ ግራ ሲጋባ ትዝ ይለኛል ።
ነፍስ ሳቅ ጀምሮ የታዘዘችኝ የሻረግ አዛኝ ያዘዝኩህን ቶሎ አልፈፀምክም ማለት ጀመረች ። ምግብ ብላ እያለች የምትለማመጠኝ የሻረግ "አሁን አይደል እንዴ የበላኸው?" ብላ መገልመጥ ጀመረች ።
ይሄን ማንነቷ አቅም ማጣት እንደደበቀባት ገባኝ ። ክፉ ልጅ ፣ የማልታዘዝ ፣ የምሳደብ አይደለሁም ለምን ጠላቺኝ እላለሁ ?
እናቴ ክፉ አልነበረችም ፣ ስትቆጣት ፣ ስትሰድባት ፣ ስታመናጭቃት አይቼ አላውቅም ለምን እንዲ በብርሃን ፍጥነት ተቀየረችብኝ??
በየምክንያቱ ሰራተኛህ መሰልኩህ ትላለች?
የየሻረግ ባህሪ መቀየሩ ከእኔ ችግር ስለሚመስለኝ እንደ ድሮ ጥሩ እንድትሆንልኝ በልጅነት አቅሜ እዳክራለሁ ። ያገኙትን ማጣት ከባድ እንደሆነ የሻረግ ሰጥታኝ የነበረውን እንክብካቤ ስትነጥቀኝ ነው የገባኝ ።
አባቴ ለውጡን እንዴት አያይም ?
አንድ ልጁን እንዴት አሳልፎ በዚህ ደረጃ ይሰጣል እል ነበር ።
አቤቱታ የማቀርብበት ግራ ስለሚገባኝ ምን ብዬ ፣ እንደምከሳት ግራ ስለሚገባኝ እንደ እሷ ቃላት ደርድሮ ማውራት ስለማልችል ።
እንደድሮ እንድትሆንልኝ እለማመጣት ነበር ። ያዘዘችኝን ቶሎ እሰራለሁ ፤ አቆላምጣት ነበር ። እኔ እና የሻረግ ቦታ ተቀያየርን ፤ እኔ ሰራተኛ እሷ እመቤት!
የሆነ ቀን ግቢያችን ውስጥ ወደቀች ፤ ስትሮክ ነው ተባለ ፤ የየሻረግ እጅ እና እግር እምቢ አለ ። የሻረግ ያኔ ሌላ ሆነች ፣ ምስኪን ሆነች ፣ አልቃሻ ሆነች ፣ ፀላይ ሆነች ፣ ተለማማጭ ሆነች ።
"ለግርድና ስለተሰራሽ እመቤትነት አልቻልሽበትም ነበር" እላት ጀመር ። "እባብ ልቡን አይቷ እግር ነሳው" እላት ጀመር ።" ተስፋም የለሽ እንዲ ሽንክልክል አልሽ ። ከዚህ በኋላ እግር እና እጅሽ እንደ እናቴ ሞቷል" እላታለሁ ።
የሻረግ ክፉ አትናገርም ነበር !
የድሮዋ የሻረግን : ትሁቷ የሻረግ ፣ ዝመተኛዋ የሻረግ ተለማማጯ የሻረግ ተመለሰች ። አለም ላይ እንደሁኔታው ራሱን እየቀያየረ እንደሚተውን የሚያክል ክፉ የለም !!
እያቆላመጥኩ አሾፍባታለሁ ፣ የማትወደውን ሙዚቃ ከፍ አድርጌ እየከፈትኩ እረብሻታለሁ ፣ ጓደኞቼ ሲመጡ ተዋወቋት የሻረግ ትባላለች
ሰራተኛችን ነች ፤ ቲያትርም ትሞክራለች እያልኩ አስተዋወቃታለሁ ።
ምኔን ነክታኝ ነው እንዲህ የቀየረችኝ ግን ??
ነገሩ ....
የክፉ ሰው ክፋት መበደሉ ብቻ አይደለም ማክፋቱ ጭምር እንጂ !!