ከመፅሐፉ ውስጥ የተወሰዱ
*የእውነት መበልፀግ ማለት በትንሹ መርካት አይደለም፡፡ ማንም ቢሆን የበለጠ መጠቀምና ማጣጣም እየቻለ፣ በትንሹ መርካት የለበትም፡፡ ምን አለፋችሁ --- በትንሹ መርካት ሃጢያት ነው! የተፈጥሮ ዓላማ፣ የሀይወት እድገትና ብልፅግናን እውን ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለህይወት አቅምን፣ ሞገስን፣ ውበትንና መትረፍረፍን ለማጎናፀፍ የሚያግዙ ነገሮች ሁሉ ሊኖሩት ይገባል፡፡ ለምን ቢሉ --- ሁሉም የመበልፀግ መብት አለውና፡፡
*ተፈጥሮ የተሰራችው ህይወትን ለማሳደግ ነው፡፡ የሚያነሳሳት ዓላማም ህይወትን የማሳደግ ፍላጎት ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለህይወት ምቾት የሚሰጥ ነገር ሁሉ ተትረፍርፎ ይቀርባል፡፡ ፈጣሪ ራሱን መቃረንና የራሱን ሥራዎች ማውደም ካልፈለገ በቀር፣ የምንም ነገር ችግር ወይም እጥረት አይፈጠርም፡፡
*እናንተ ስለድህነት አታውሩ፤ ስለድህነት አትመራመሩ፤ ስለድህነት አትጨነቁ፡፡ የድህነት መንስኤ አያሳስባችሁ፡፡ ድህነትን ጉዳያችሁ አታድርጉት፡፡ እናንተን አይመለከታችሁም፡፡ እናንተን የሚመለከታችሁ መፍትሄው ነው - መድሃኒቱ! በርትታችሁ ሃብታም ሁኑ! ድሃውን ለመርዳት የተሻለው መንገድ ራስን ማበልፀግ ብቻ ነው::
*ህልማችሁን እውን ለማድረግ የሚስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ በውስጣችሁ አለ፡፡ ተነግሮ የማያልቅ፤ የትየለሌ አቅም አላችሁ፡፡ የፈጠራ አቅም የለንም ብትሉም ፤ ቀደም ሲል ሳይሳካላችሁ ቢቀርም፤ ሁሉንም ሞክራችሁ ምንም የቀራችሁ እንደሌለ ብታስቡም እንኳን —— ለዚህ መፅሃፍ አዕምሮአችሁን ከፈቱ፡፡