የሰው ልጅ ምኞት ገደብ የለሽ ነው። ምኞት በጥም የተቃጠለ ሰው የሚጠጣው ጨዋማ ውሃ ነው፤ ጨዋማ ውሃ የውሃ ጥምን አለማርካት ብቻ ሳይሆን ጥሙ እየጨመረ እንዲሄድ ማድረጉ የማይቀር ነውና። ስለዚህ የሰው ልጅ የእርካታ ምንጩ ከውስጡ ነው፤ በምኞቱ አለመርካት ሳይሆን ስቃዩም እየጨመረ ይሄዳል። እናም ለምኞትህ ልጓም አበጅለት። ምኞትህ በጨመረ ቁጣህ ደስታና እርካታህ እየቀነሰና እየከፋ ከመሄዱም ባሻገር መጨረሻህ ወደ እብደት መድረስ ብቻ ይሆናል።
ሰዎች ሞኞታቸውን ለማርካት ዘወትር ሲሮጡ ስንመለከት ውጤታቸውም አንዱ ከሌላው ማሴር፤ አንዱ ሠራዊት በሌላው ሰራዊት ላይ ማዝመት፤ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ መነሳት፤ ወንድም በወንድሙ ላይ ለጥፋት ማድባትና ወዳጅ የወዳጁን መቃብር መቆፈር ናቸው። በአጭሩ እርስ በእርስ መጋደልና መጠፋፋቴ የዘወትር ተግባራቸው ይሆናል።
ልብ በሉ ሰዎች ሕይወታቸው የሚያልሙበትም ሆነ የሚያጠፉበት ዋነኛ ምክንያት ምኞታቸው ነው። ማታለል፣ መስረቅ፣ ዝሙት፣ ከዚያም ተይዞ በውርደትና በሐፍረት መሰቃየት የምኞታቸው ዘር የሚያሳጭደው አዝመራ ነው። በራሳቸው ገላና ቃል ኃጥያትን ይፈጽማሉ!። በአዕምሮአቸው የሚፈጽሙት ኃጥያት መጨረሻው በሥጋና ነፍሳቸው ሐዘንና መከራ እንደሚያተርፍላቸው ቢያውቁ እንኳን ይኸንኑ ከመፈፀም ወደኋላ አይሉም። መጨረሻቸውም በመከራ ዓለም ገብቶ በዚያም መስጠም ይሆናል።
እናም ከምኞት እራቁ፤ ምኞት በጥም የተቃጠለ ሰው የሚጠጣው ጨዋማ ውሃ ነው..
፦ Siddhartha Gautama
- The Life and times of the awakened 📖