አንዳድ ጊዜ ብቻችሁን ሁኑ!
በመጀመሪያ ለብቻ በመሆንና በብቸኝነት መካከል ልዩነቱን እንወቅ፡፡
ለብቻ መሆን ማለት አንድ ተግባርና ልምምድ ነው፡፡ በራስ ፈቃድና ሆን ተብሎ ከሰዎች ገለል ያለ ቦታና ጊዜ መርጦ ከራስ ጋር ማሳለፍ ማለት ነው፡፡ ለብቻ ለመሆን የግድ በአካልም ሆነ በማሕበራዊ ሚዲያ ከሰዎች ለየት ማለትን ይጠይቃል፡፡
ብቸኛ መሆን ማለት ተግባር ሳይሆን ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት የሚመጣው በእኛ ፈቃድ ሳይሆን በውስጣችን ካለው የምልከታና የስነ-ልቦና ቀውስ ነው፡፡ ብቸኝነት ስሜት እንዲሰማን የግድ ከሰው በመለየት ብቻችንን መሆን የለብንም፡፡ በሰዎች መካከል እየኖርን እንኳን ይህ ስሜት ሊያጠቃን ይችላል፡፡
• ከእለት እለት ከሰዎች ጋር የምታሳልፉ ከሆነና አንድም ቀን ለብቻችሁ የምታሳልፉበት ጊዜ ከሌላችሁ . . .
• ሁል ጊዜ ከሰው ጋር ካልሆናችሁ የሚጨንቃችሁ ከሆነ . . .
• በአካል ከሰዎች ጋር ካልሆናችሁ የግድ ሶሻል ሚዲያ ላይ የምታሳልፉ ከሆነ . . .
• ብቻችሁን ስትሆኑ የብቸኝነት ስሜት የሚያጠቃችሁ ከሆነ፡፡
ከላይ የተጠቀሱትና መሰል ስሜቶች እንዳለባችሁ የምታስቡ ከሆነ ብቻችሁን የመሆን ልምምድ እንደሌላችሁና የለብቸኝነት ስሜት ተጋላጭ እንደሆናችሁ አሳባቂ ሁኔታ ነው፡፡
ለብቻችሁ ከራሳችሁ ጋር ጊዜን ማሳለፍ ለብዙ ነገር ይጠቅማችኋል፡፡
• ከሰዎች አመለካከት አጉል ተጽእኖ ነጻ በሆነ መልኩ ውስጠ-ህሊናችሁን እንድታደምጡ፣
• ተረጋግቶ ስለወደፊት ለማቀድ፣
• ከሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማመዛዘን፣
• ምቾት የማይሰጡ ስሜቶች የፈጠሩባችሁን ሁኔታዎች ለይቶ በማወቅ ለማስተካከል
እና ለመሳሰሉት ስኬታማ ልምምዶች ይጠቅማችኋል፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ ለብቻችሁ ያሳለፋችሁት መቼ ነው?
በየስንት ጊዜው ለብቻችሁ የመሆን ልምምድ አላችሁ?
ይህንን ልምምድ ዛሬውኑ ለመጀመር ብትወስኑ ምን ይመስላችኋል?
Dreyob