💡 አዋጭ የንባብ ስልቶች ለ Entrance Exam ዝግጅት ( ውጤታማ ከሆኑ የግቢ ተማሪዎች ተሞክሮ) እና ከ Educational Psychology ጥናቶች አኩያ
መቅድም ፥
ለአይምሯችንን በተገቢው መንገድ በመጥቀም ለፈተና ከመዘጋጀት አኳያ ከግምት ውስጥ ማስገባት ከሚገቡን ብዙ ነገሮች አሉ ። እስቲ የሚከተሉትን ነጥቦች እንመልከት ፡
• አብዛኛው የአእምሯችን የማሰብ እና የማስታወስ አቅም በቀላሉ የሚገነባ አደለም
• የምናነብበት መንገድ ቀላል በሚሆንበት ጊዜ ሊረሳበት የሚችልበት እድል የሰፋ ነው ።
• የሚከብዱንን እርዕሶች እና ሃሳቦች ላይ ለፈተና መዘጋጀት መሞከር ተስፋ ሊያስቆርጥ ይችላል ፤ ይሁን እንጂ እነዚህን ነገሮች ለማስተካከልና ጥሩ ችሎታ ለማግኘት የግድ ጫናውን ተጋፍጦ መዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
• ጥያቄ ስትሰሩ መልሱን ወይም መፍትሄውን ከማየትችሁ በፊት በተለየ መልኩ ለማስብ ብትጥሩ የተሻለ ትማራላችሁ።
• ያለ እረፍት ለማንበብ መታገሉ ፣ መሸምደድ እና ደጋግሞ ማንበብ አያዘልቅም!
በአይምሯችን ውስጥ ያሉ የዕውቀት ክምችቶችን በአንድ ደን እንዳሉ ዛፎች አስቧቸው። ከአንድኛው ቦታ ወደ ሌላኛው ቦታ በተመላለሳችሁ ቁጥር እንዴት እዛ ቦታ መድረስ እንዳለባችሁ እየገባችሁ ይመጣል። ችግሩ ግን ፈተና ላይ በዚህ በምታውቁት መንገድ እንድትሄዱ አትጠየቁም ፣ ፈተና እንደ ስሙ ፈተና ነው እና ፣ የምታውቁትን እና የለመዳችሁትን መንገድ ዘግተው ሌላ ትክክለኛውን አቅጣጫ ፈልጋቹ ድረሱ ትባላላችሁ። ስለዚህ ጎበዝ ተማሪ ሃላፊነቱ ከፈተናው በፊት በ ደን ውስጥ ያሉትን መግቢያ እና መውጫ አማራጮች ጠንቅቆ ማውቅ ነው ማለት ነው። ለዚህ ነው ጎብዝ ተማሪዎችን ንባብ እንዴት ነው ብላችሁ ብትጠይቋቸው እንደሚከብድ የሚነግሯችሁ ፣ ምክንያቱም ሮጠው ያቺን ደስ የምትለዋን እርዕስ አይደለም ከላይ ከላይ የሚያነቡት ፣ ውስጥ ድረስ ይገባሉ ፣ በኋላ ፈተናው እንዲቀላቸው አሁን ከባድ ነው ያሉትን ነገር በሙሉ ይጋፈጣሉ። ይህን ካልን አሁን አዋጭ ወደ ሆኖ የንባብ ስልቶች ዝርዝር እንለፍ!
1️⃣ Practice Testing ( የመለማመጃ ፈተናዎች)
High school እያለው አንድ መምህሬ ሶስት ጊዜ ከማንበብ 1 ጊዜ ጥያቄ መስራት ይል ነበር። ጥያቄ መስራት የገባችሁን እና ያልገባችሁን ቦታ ለመለየት እድል ስለሚሰጣችሁ ፣ ግር ያላችሁ በነቂስ መርጣችሁ ጊዜ በመቆጠብ እንድታነቡ ያግዛችኋል። ምንም እንኳን በ ደን ውስጥ ስላለ ስለሆነ ቦታ ቢያወራም ፣ ከ Note የሚለየው ቦታው ጋር ልትሄዱበት የምትችሉበትን የተለያየ አቅጣጫ ማሳየት መቻሉ ነው። በ አንድ ድንጋይ አራት ወፍ መምታት እየተቻለ አንድ ውፍ - ሼ ነው።
2️⃣ Active Recall ( አብሪ ማስታወሻ)
ልክ እያነበባችሁበት ባለበት ፣ የተለየ ሃሳብ ውስጥ የሚከታችሁ ነጥብ አለ አደል? ከዚህ በሗላ ምንድነበር ያለው የምትሉት?" ከዚህ ጋር አብሮ የሚመጡ ነገሮች ምንድናቸው 5 ነበሩ ብላችሁ" አይምሯችሁ ላይ ሲያቃጭሉ የምታስቧቸው ! "ጣይቄው እንዲህ ሲሆን መከተል ያሉብን ሁለት ህጎች አሉ" ፣ ብላችሁ እንድታስቡ የሚያረጓችሁ ሃሳቦች እንደዛ አይነት ሁኔታ ውስጥ ስትሆኑ ፣ ሮጣችሁ ኖት ላይ ለማረጋገጥ አትሂዱ ፣ ራሳችሁን ገድቡት እና ሃሳቡ ሲመጣ አይምሯችሁን ፈትሹት ፣ የውሻ ጥርስ አጥንት በመታገል ነው የሚጠነክረው ፣ በጭካኔ የመጣው ቢመጣ ንክስ ፣ አይምሯችሁን አስጨንቁት ፣ ይህንን ስንል 10 ደቂቃ ሙሉ የሆነ ነገር ሲከብዳችሁ አፍጥጣችሁ እያያችሁት እዘኑ ማለታችን አደለም። 9 Factors of this issue የሚል ነገር ስታዩ ለምን ዝርዝሩ ላይ ትሄዳላችሁ ፣ መጽሃፉን ከድናችሁ ፣ በአይምሯችሁ በማስታውስ ሁሉንም ለመዘርዘር መሞከር ከዛን ማስተያየት። ይህን ስታረጉ ኖታችሁን በቀይ ቀለም እየቀባችሁ ካነበባችሁት በላይ በቂ ዝግጅት ኖራችሁ ማለት ነው ።
3️⃣ አይምሮን በከባድ ሚዛን መፈተን
የሰራችሁት ጥያቄ ደግማችሁ ምስራት ደስ ይላል አደል ? አዳዲስ ማቴሪያል ከማንበብ ይልቅ ድሮው ያነበባችሁትን ምስመር በመስመር ስታነቡ ቀላል ነው። ካነበባችሁ በኋላ ጥያቄ ስሰሩ መጀመሪያ ላይ ያሉትን ቀላል ጥያቄዎች ለኮፍ ለኮፍ አርጋችሁ መጨረሻ ላዩ የሚኖሩትን ከባባድ ጥያቄዎች ለማን የተዘጋጁ ይመስላችኋል? ለ ግቢ ተማሪዎች ወይስ ለመምህራን! አሰልቺ የሆኑ እና ግራ የሚያጋቡ ርዕሶችን ማንበብ አድካሚ ሊሆን ይችላል ግን ደግሞ የሚሰማችሁ ጥሩ ያልሆነ ስሜት እየተገላችሁ እና እየለፋችሁ እንደሆነ የምትረዱበት እንጂ የ ወድቀታችሁ ማሳያ አደለም።
4️⃣ ክፍተት መስጠት ( SPACING)
በጣም ትልቅ የሆነ አይምሮን ሃይልን የሚወስዱ ንባቦችን ስታነቡ ምናልባት ደስ ብሏችሁ ዛሬ ከዚህ ለአፍታ እንኳን ሳልነሳ ጭርሼ ውላለው ልትሉ ትችላላችሁ ፣ እንዲህ እያረጋችሁ ለትንሽ ቀናት ሊሳካ ይችላል ፣ ከዛን ግን አይምሯሁ ዝሎ ንባብ የሚባል ነገር እርም ብላችሁ ስተውት ትዝ ይላችሁኋል? አይምሯችሁም አይናችሁም እንዲያርፍ ፍቀዱለት ፣ ለ 2 ወይም ከ ሶስት ሰዓት ንባብ በኋላ ፣ ከተቀመጣችሁበት ተነሱ ፣ የተፈጥሮ photon Energy እያገኘ አይናችሁ እንዲዝናና ፍቀዱለት ፣ ለመሳቅ ለመጫወት ሞክሩ ! ምክንያቱም አይምሯችሁ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥሉትም ቀናት ስለሚያስፈልጋችሁ።
5️⃣ ንባብን በነጻነት ማጣመር
አንድ አይነት እርዕስ ለመጨረስ ወይም አንድ Subject ላይ አይምሯችሁን አትገድቡት ፣ History ላይ ያነበባችሁት a battle of "some site " ምናልባትም Geography Class ደግሞ የ Mineral site ሊሆን ይችላል ፣ 9ኛ ክፍል ያነበባችሁት 11ኛ ክፍል ላይ ካለ ሁለቱንም መፅሃፍ ዘርግታችሁ አንድ ላይ አጣምሯችሁ ለማንበብ አትፍሩ። ነባባችሁ የግድ ደባሪ መሆን የለበትም ጥሩ ውጤት ለማምጣት ፣ Chemistry ያነበባችሁት ርዕስ Biology እንድታነቡ ከገፋፋችሁ ሂዱ አንብቡ ፣ በንባብ ፍቅር ተጠመቁ ፣ ውስጣችሁን እንዲወራችሁ ፍቀዱለት ፣ የንባብ ፍላጎታችሁን ለስኬታችሁ ተጠቀሙበት።
6️⃣ ሁሌም ንቁ መሆን
ይሄን ብሔራዊ ፈተና ጥሩ አርጎ ለምስራት እየተጋ ያለው ጓደኛችሁ ጋር ደውሉ ፣ ወይ የትምህርት ቤት አማካሪያችሁ ወይ ደግሞ የምትግባቡት መምህር ጋር ፣ አሁን እየሄዳችሁበት ካለበት ብቃት ብላይ ልትሄዱበት የምትችሉበትን ርቀት ጠይቋቸው። በፍጹም የአሸናፊነት ወይ ደግሞ የውሸጥ ድል ስሜት እንዲያዘናጋችሁ አትፍቀዱ ፣ በአቅራቢያችሁ ሁሉ ያሉት ብዙ መልፋት እንደማይጠበቅባችሁ ሲነግሯችሁ ፣ ተዘናግታችሁ በስንፍና እንዳትሰናከሉ ከልብ ትቢት ተጠበቁ
7️⃣ ማስታወሻ ዘዴን ማዳበር
ሊረሱ የሚችሉ ሃሳቦችን ልታስታውሱበት የምትችሉባቸውን ዘዴዎች በመፍጠር ለምዝናናት ሞክሩ ፣ ምናባዊ በሆነ መልኩ በግጥም ፣ ወይ በ acronyms ወይ በ Diagram አግናኝታችሁ ለመረዳት ሞክሩ።
@Entranceprepare
@Entranceprepare
To register in our special tutorial program👇
@Epregisterbot