38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ላስተባበሩ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 19/2017 ዓ.ም (Ethiopian Media Authority)
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመዘገብ የመጡ ጋዜጠኞችን ላስተባበሩ የተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ-ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን ዶ/ር፤ የተቋሙ ተልዕኮ እውን ከማድረግ አንፃር ባለሙያዎቹ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመዘገብ ለመጡ ጋዜጠኞችን ከማስተባበርና ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንጻር ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
የተሰራው ስራ ገጽታ ከመገንባት አንጻር ሚናው የላቀ መሆኑን ገልፀው፤ ለዚህ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ቀጣይ እንደ ቷቋምና እንደ ሀገር በሚሰሩ ስራዎች ላይ ይህንን መሰል የስራ ተነሳሽነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ባለሥልጠኑ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለመዘገብ ለመጡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ባደረገው ተሳትፎ ዙሪያ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ ጉባዔውን ሽፋን ለመስጠት ከ አንድ ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ የሚዲያ አካላትና ጋዜጠኞች ሙሉ አገልግሎት እንደተሰጠ ተገልፃል፡፡
የ38ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚዲያ አካላትን ላስተባበሩ የተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡