አብያተ እምነት የሰማያዊ መንግሥት ተልዕኮ ማስፈጻሚያ ኤምባሲዎች በመሆናቸው ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
የብልጽግና መንግሥት የወንዝ ዳር፣ ጫካ፣ ኮሪደር… ወዘተ ፕሮጀክት በሚሉ መጠሪያዎች የሚያከናውነውን የማናለብኝነት ፈረሳና የማፈናቀል ተግባር አስመልክቶ በቅርቡ የአገራችን የበላይ ሕግ የሆነውን ሕገ መንግሥትና የሚመለከታችውን አዋጆች ጠቅሰን በትብብር ፓርቲዎች የጸና አቋማችንን መግለጻችን ይታወቃል።
ከዚኹ የኮሪደር “ልማት” ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች የአምልኮ ሥፍራዎች ሕጋዊ ይዞታዎች ድንበር በማን አለብኝነት እየፈረሰ እንዳለና እንደሚፈርስ ማስጠንቀቂያ እንደደረሳቸው መገንዘብ ችለናል።
እየፈረሱ ካሉት በዋቢነት የሰበታ ጌቴሴማኒ ቤተደናግል ጠባባት የሴቶች ገዳም ይዞታ ከክብር በወረደ አኳኋን እንዲፈርስ የተደረገ ሲሆን ከየካቲት ፲፪ አደባባይ ከፍ ብሎ ያለውና ከአምስቱ ዓመት የፋሽስት ጣልያን ወረራ ወቅት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥ ታሪክ ያለው የአገር ባለውለታው የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ይዞታም ጠባብ የሆነውን ዐውደ ምሕረት የበለጠ በማጥበብ ከፊት ለፊቱ የገዳሙና የገዳሙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ፈረሳ እንደሚከናወንባቸው ፓርቲያችን መረጃ ደርሶታል።
እነዚህን በዋቢነት ጠቀስን እንጂ ፈረሳው ያነጣጠረባቸው በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው የሚገኙ አብያተ እምነት ቁጥር ብዙ እንደሆነ ተረድተናል።
ባለፉት ጥቂት ተከታታይ ዓመታት በአብያተ ክርስቲያን፣ መሳጅዶች ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የደረሱ ቃጠሎዎች፤ በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ የደረሱ አሰቃቂ ግድያዎች በኢትዮጵያ በትልቁ አገራዊ እሴታችን (ሃይማኖት) ላይ የተጋረጠውን ኹለንተናዊ ጥቃት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
ከዚኹ የቀጠለ በሚመስል አኳኋንና በተቀናጀ መልኩ በአዲስ አበባና አካባቢው አብያተ ክርስቲያን ይዞታዎች ላይ እየተወሰደ ያለው የማፍረስ ተግባር ከውጭና ከውስጥ ተናቦ የሚተገበር መኾኑን መጠርጠር አያዳግትም።
አብያተ እምነት ለሰው ልጅ አጠቃላይ መንፈሳዊና አእምሯዊ ልዕልና ያላቸው ሚና አይተኬ ነው። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያውያን ሲሆን ድርብ እውነት ያደርገዋል።
እነዚኽ የእምነት ተቋማት እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው የሚኖሩ በአማካይ ሃያ ሺህ ያክል ዜጎችን የሚያገለግሉ እንደሆነ የሚገመት ሲሆን በዚኽ ልክ የዕለት ተዕለት አገልግሎት የሚሰጡ ሌሎች ተቋማትን መጥቀስ አይቻልም።
አውሮፓውያን በዘመነ አብርኆት(enlightenment) ሃይማኖትና አብያተ እምነትን አሽቀንጥረው ጥለው ነበር። ሆኖም ባለፉት ፶ ዓመታት በተለይ የደረሰባቸውን የሞራል ኪሣራ፣ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ፣ ስግብግብነት፣ እርካታ ማጣት፣ ግለኝነት፣ የተዘወተረ ራስን ማጥፋትና መሰል ዘግናኝ ድርጊቶች በሕዝባቸው ላይ መንሰራፋት አካሄዳቸውን ቆም ብለው እንዲያጤኑ አስገድዷቸዋል።
የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት አብዮተኞች እንዲኹ ቅጽር መዳፈር፣ ማፍረስ፣ አሻራቸውን ማጥፋት፣ መጽሐፍትን ማቃጠል፣ የሃይማኖት አባቶችንና ምዕመናንን ማሳደድ በሰፊው ሞክረውት ነበር።
ያ ኹሉ አልፎ ወደቀልባቸው የተመለሱ መሪዎች ሲመጡ ዛሬ ሕዝባቸውን የሃይማኖትና ሞራል ልዕልና ያለው በስልጣኔ ስም ለሚመጣ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት "አይሆንም" ባይ በማድረግ እንዲያውም የዓለሙን ሚዛን በማስጠበቅ ይጠቀሳሉ።
በአገራችን ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአብያተ እምነት እና በምእመናን ላይ እየደረሰ ያለው ተከታታይ ጥቃትና የመግለጫችን ጭብጥ የሆነው በአብያተ እምነት ይዞታዎች ላይ ያነጣጠረ የማፍረስ ዘመቻ ይኸው “ያደገው” ዓለም ያለፈበት የጥፋት ጎዳና አገራዊ መገለጫ ነው።
በመጀመሪያ ዙር የኮሪደር “ልማት” የተጠቀሰው የፈረሳ ሥራ መስመር ላይ ያሉ የምድራውያን የውጭ አገራት መንግሥታት ኤምባሲዎችን እንዳልነካቸው ኹሉ ይልቁን እነዚህን የሰማያዊ መንግሥት ኤምባሲ ሆነው የሚያገለግሉ ተቋማት የፈረሳው ሥራ ፈጽሞ እንዳይነካቸው እናት ፓርቲ በአጽንኦት ያሳስባል።
በብልጽግና መንግሥት የአብያተ እምነት ይዞታዎችን በማፈራረስ የሚተገበር የትኛውም ሥራ እንደ ማንኛውም ምድራዊ መንግሥት የሥርዓቱ እድሜ አብቅቶ በሌላ ሲተካ ወደ ቀደመ ይዞታቸው መመለሳቸው አይቀሬ ነው።
በደርግ ዘመን ዋናው መግቢያ ተዘግቶ ቆይቶ ኢሕአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት የተከፈተውን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያስታውሷል።
ስለሆነም የብልጽግና መንግሥት ከዚኽ ነባር ሃይማኖት ጠል አካሄዱ እንዲታቀብና የአብያተ እምነት ቅጽሮችን ማፍረሱን በአፋጣኝ እንዲያቆም በጽኑ እናሳስባለን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፲፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ