#RemedialExam
የ2017 ትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ከማዕከል የሚሰጥ ፈተና ከግንቦት 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሜጄና (ዶ/ር) በቀን መጋቢት 15/2017 ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፉት ሰርኩላር፤ የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ግምገማ ከ100% ከማዕከል እንደሚሆን አስታውሰዋል፡፡
የሪሚዲያል ተማሪዎች ከዚህ በፊት 70% በማዕከል እና 30% በተቋማት የሚዘጋጁ ምዘናዎችን ይወስዱ የነበረ ሲሆን፤ ከ2017 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የሪሚዲያል ተማሪዎች የማጠቃለያ ምዘና ከ100% ከማዕከል እንዲሰጥ በጥቅምት 2017 ዓ.ም መወሰኑ ይታወሳል፡፡
በዚህም የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በሚማሩበት ተቋም የሚሰጥ የተከታታይና የማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ከዛም በማዕከል በሚሰጥ ፈተና የተማሪዎቹ መቀጠል እና አለመቀጠል የሚወሰን ይሆናል፡፡
እንዲሁም የሚካተቱት ኮንቴንቶች ከአዲሱ ሲላበስ ለ 12 ብቻ ፤ ከድሮው ሲላበስ ደግሞ ከ9-11 ያሉትን የሚያካትት ነው ። ተማሪዎቹ ሀይስኩል ላይ ያልተማሩትን አንፈትንም ተብሏል ።
Via: Remedial Tricks