አርቴታ ከክለቡ ባለቤቶች ጋር ውጥረት ውስጥ ገቡ !
የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በዝውውር ጉዳዮች ከክለቡ ባለቤቶች ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አርሰናል በጥር የዝውውር መስኮት የፊት መስመር አጥቂ አለማስፈረሙን ተከትሎ በክለቡ ባለቤቶች መበሳጨታቸው ተነግሯል።
መድፈኞቹ ጋብሬል ጄሱስ እና ቡካዩ ሳካን በጉዳት ሲያጡ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አጥቂ እንደሚገዛላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል እንደነበረ ተገልጿል።
ሚኬል አርቴታ ለኦሊ ዋትኪንስ 60 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንዲሆን ቢጠይቁም የክለቡ ሀላፊዎች ከ 40 ሚልዮን ፓውንድ በላይ ማውጣት አለመፈለጋቸው ተዘግቧል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ሀላፊዎች የመታለል ስሜት እንደተሰማቸው ተነግሯል።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ትላንት ስለ ጉዳዩ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “ ተጨዋች ባለመፈረሙ በጣም ተበሳጭተናል " ብለው ነበር።
https://t.me/Ethioallball