ኢትዮ ዜና ስፖርት🔴


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Sport


ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
Contact us @EEMET3
@Ethiosportnews_bot
@ethiosportnews_diskbot

ኢትዮ ዜና ስፖርት 2016 ዓ/ም

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Sport
Statistika
Postlar filtri


“ ሊጉን ለማሸነፍ ቆርጫለሁ “ ሳላህ

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ ከሊቨርፑል ጋር ፕርሚየር ሊጉን ለማሸነፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

“ ከሊቨርፑል ጋር ሊጉን ለማሸነፍ ቆርጬ ተነስቻለሁ የማይረሳ ይሆናል ድሉን ከደጋፊው ጋር ማክበር እፈልጋለሁ " ሲል መሐመድ ሳላህ ተናግሯል።

ከዚህ በፊት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቅድሚያ የሚሰጠው እንደነበር የገለፀው ሳላህ አሁን ግን ትኩረቴ ፕርሚየር ሊግ ማሸነፍ ነው ብሏል።

“ በመጀመሪያ ጨዋታዬ የገጠመኝ ከባድ ትግል እዚህ በዚህ ሁኔታ እንዴት መቀጠል እችላለሁ የአካል ብቃቴን ለማሳደግ ጂም መሄድ አለብኝ ብዬ እንዳስብ ያደረገኝ ነበር።" ሳላህ




The stage is set for the FA Cup quarter-finals 🍿


ናታን አኬ ቀዶ ጥገና አድርጓል !

የማንችስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋቹ ናታን አኬ በጉዳቱ ምክንያት ቀዶ ጥገና ማድረጉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሳውቋል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ሲቲ ከቀናት በፊት ፕሌይ ማውዝን ባሸነፈበት ምሽት ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በኋላ ናታን አኬ  ለረጅም ጊዜ ከሜዳ እንደሚርቅ ተናግረው ነበር።

አሁን ላይ ናታን አኬ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ ወራት እንደሚወስዱበት ተገልጿል።


https://t.me/Ethioallball


አርሰናል ሀላፊ ለመሾም ተቃርቧል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በኤዱ ጋስፐር ምትክ አዲስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመሾም መቃረቡ ተገልጿል።

መድፈኞቹ የቀድሞውን የአትሌቲኮ ማድሪድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ ለመሾም መቃረባቸው ተነግሯል።

በአለም እግርኳስ ውስጥ ስማቸው በጉልህ የሚነሳው አንድሬ ቤርታ ከኤሲ ሚላን ጥያቄ ቀርቦላቸው ለአርሰናል ቅድሚያ መስጠታቸው ተገልጿል።

ጣልያናዊው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አንድሬ ቤርታ በአትሌቲኮ ማድሪድ ቤት ከአሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ ጋር ለአስራ ሁለት አመታት የሰሩ ናቸው።

https://t.me/Ethioallball


“ እኔ የዋህ አይደለሁም “ ሩበን አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም “ እኔ የዋህ አይደለሁም “ ሲሉ ዋይን ሩኒ ለሰጠው አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል።

ዋይን ሩኒ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ሩበን አሞሪም ዋናው አላማችን ሊጉን ማሸነፍ ነው ማለታቸውን በዚህ ሁኔታ ይሄን ማሰብ የዋህነት ነው ሲል ገልፆ ነበር።

“ እኔ የዋህ አይደለሁም “ ሲሉ ምላሽ የሰጡት ሩበን አሞሪም ለዚህም ነው በ 40ዓመቴ ማንችስተር ዩናይትድን የማሰለጥነው ብለዋል።

“ አላማችን ሊጉ ነው ምናልባት ከእኔ ጋርም ላይሆን ይችላል ፤ የክለቡም ሆነ ቦርዱ አላማ የቀድሞው የዋንጫ አሸናፊነት መመለስ ነው “ አሞሪም


ዩናይትድ ከኤፌ ካፕ ውድድር ተሰናበተ !

ፉልሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የኤፌ ካፕ አምስተኛ ዙር ጨዋታ በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ግቦችን ለማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እንዲሁም ለፉልሀም ካልቪን ባሴይ ማስቆጠር ችለዋል።

በመለያ ምት በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ቪክቶር ሊንድሎፍ እና ዚርኪዜ ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዘመኑ ከየትኛውም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች በበለጠ ሀያ አራት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

የኤፌ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ከደቂቃዎች በኋላ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል።


ተጠናቀቀ

ማንችስተር ዩናይትድ 1 - 1 ፉልሀም

⚽ ፈርናንዴዝ                   ⚽ ባሴይ

⏩ ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ በአቻ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰዓት አምርተዋል።


እረፍት

ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ፉልሀም

                   ⚽ ባሴይ


“ እኛ ከሊቨርፑል አናንስም “ ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው በሊቨርፑል ጨዋታ አጥቅቶ እንደሚጫወት ገልጸዋል።

“ ሊቨርፑልን በደንብ አውቀዋለሁ ምናልባት በአሁኑ ሰዓት የአውሮፓ ምርጡ ቡድን ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም “ ነገርግን እኛ ወደኋላ ተመልሰን በመከላከል ላይ የተመሰረተ ጨዋታ የመጫወት ፍላጎት የለንም “ ብለዋል።

" ሊቨርፑልን አጥቅተን እንጫወታለን ምክንያቱም እኛ ከእነሱ ያነስን አይደለንም “ ሉዊስ ኤንሪኬ

ፒኤስጂ የፊታችን ረቡዕ ከሊቨርፑል ጋር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋል።


ሜሲ ባለመኖሩ ደጋፊዎች ይቅርታ ተጠየቁ !

የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ ዛሬ ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት ወደ ቴክሳስ በማምራት ከሂውስተን ጋር የሜጀር ሊግ ሶከር ጨዋታውን ያደርጋል።

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ በአሰልጣኙ እረፍት የተሰጠው መሆኑን ተከትሎ በጨዋታው አይሳተፍም።

ይህንንም ተከትሎ የኢንተር ሚያሚ ተጋጣሚ ቡድን ሂውስተን ሊዮኔል ሜሲ ይሳተፋል ብለው ጨዋታውን ለመታደም ትኬት የቆረጡ ደጋፊዎቹን ይቅርታ ጠይቋል።

የክለቡ ደጋፊዎች የሊዮኔል ሜሲን ወደ ስፍራው አለማቅናት ዜና ሲሰሙ በመሳጨታቸው ተነግሯል።

ስለ ተጋጣሚ ቡድን አሰላለፍ መወሰን አንችልም ያለው ክለቡ በመግለጫው ደጋፊዎቹ ለማካካሻ እንዲሆናቸውም ነፃ ትኬት ማቅረቡን ገልጿል።

ሊዮኔል ሜሲ የለም ብለው ሳይቀሩ የምሽቱን ጨዋታ የሚታደሙ ደጋፊዎች በትኬቱ የወደፊት ጨዋታ በነፃ እንዲመለከቱ መወሰኑን ክለቡ አሳውቋል።


“ ለቀጣዩ አመት ጠንካራ ዝግጅት ጀምረናል “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ክለቡ ለቀጣዩ የውድድር አመት ከወዲሁ ጠንክሮ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

ስለ ቀጣይ ዝውውር ያነሱት ሩበን አሞሪም “ ተጨዋቾች ለመግዛት ተጨዋች መሸጥ አለብን ያለንበትን ሁኔታ እናውቀዋለን “ ብለዋል።

“ በዋናው ቡድናችን እና የታዳጊዎች አካዳሚ በርካታ ነገሮችን በመቀየር ላይ እንገኛለን “ ሲሉ ሩበን አሞሪም አስረድተዋል።

" በአሁኑ ሰዓት በርካታ ነገሮችን እየሰራን ነው ለሚቀጥለው የውድድር አመት ከወዲሁ የተሻለ ጠንካራ ዝግጅት ተጀምሯል “ ሩበን አሞሪም


አሌሀንድሮ ጋርናቾ ቡድኑን ይቅርታ ይጠይቃል !

የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኢፕስዊች ታውን ጨዋታ ላሳየው ባህሪ ቡድኑን እራት በመጋበዝ ይቅርታ እንደሚጠይቅ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ገልጸዋል።

ጋርናቾ በጨዋታው ዶርጉ በቀይ መውጣቱን ተከትሎ በማዝራዊ ተቀይሮ የወጣ ሲሆን ቀጥታ ወደ መልበሻ ቤቱ ሲገባም ተስተውሎ ነበር።

" ትላንት ጠዋት ቢሮዬ መጥቶ ነበር " ያሉት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ምንም ችግር የለም ቡድኑን እራት ይጋብዛል ብለዋል።

ጋርናቾ ስላደረገው ነገር ምርመራ ማድረጋቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ ልብሱ ረጥቦ ስለነበር መልበሻ ቤት ቀይሮ ጨዋታውን ከዛው እንደተከታተለ አረጋግጫለሁ ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትኩረት የሚደረግበት በመሆኑ ግንዛቤው እንዲኖረው አስረድቼዋለሁ ብለዋል።


አሊዮ ሲሴ በሀላፊነት ሊሾሙ ነው !

የቀድሞ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ አዲስ ብሔራዊ ቡድን በሀላፊነት ሊረከቡ መሆኑ ተገልጿል።

ሴኔጋላዊው አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ በአሁኑ ሰዓት የሊቢያ ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

በስምምነቱ መሰረት አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ ከዋናው ብሔራዊ ቡድን በተጨማሪ ወጣት ቡድኑን ለመከታተል ሀላፊነት መቀበላቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ በሚቀጥለው ወር መጀመሪያ ጀምሮ ብሔራዊ ቡድኑን ተረክበው ሥራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

https://t.me/Ethioallball




“ ፈርናንዴዝ ባይኖር ወራጅ ቀጠና ነበሩ “ ኢያን ራይት

በተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው የቀድሞ የአርሰናል ተጨዋች ኢያን ራይት ማንችስተር ዩናይትድ በአሁኑ ደረጃ ያለው በብሩኖ ፈርናንዴዝ ብርታት መሆኑን ገልጿል።

ኢያን ራይት ሲናገርም “ ማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ባይኖራቸው በዚህ ሰዓት በወራጅ ቀጠናው ይሆኑ ነበር “ ሲል ተደምጧል።

የቀያይ ሴጣኖቹ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እንዲሁ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ " ፈርናንዴዝ ወሳኝ እና የተለየ ተጨዋቻችን ነው ነገሮች ሲከብዱን ይደርስልናል “ ብለዋል።


ፓትሪክ ዶርጉ ስንት ጨዋታዎች ያመልጡታል ?

የማንችስተር ዩናይትዱ የመስመር ተጨዋች ፓትሪክ ዶርጉ ቡድኑ ኢፕስዊች ታውንን ባሸነፈበት የምሽቱ ጨዋታ ቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወሳል።

ፓትሪክ ዶርጉ በቀጣይ ሶስት ጨዋታዎች በቅጣት ምክንያት እንደሚያመልጡት ማንችስተር ዩናይትድ ይፋ አድርጓል።

ይህንንም ተከትሎ ፓትሪክ ዶርጉ ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ

- ከፉልሀም ( ኤፌ ካፕ )
- አርሰናል እና
- ሌስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የሚያመልጡት ይሆናል።


“ ስለ ማድሪድ አጨዋወት የሚያስታውስ የለም “ ፒኬ

የቀድሞ የባርሴሎና ኮከብ ጄራርድ ፒኬ ሪያል ማድሪድ በርካታ ዋንጫዎችን ቢያሸንፍም የነበረው የአጨዋወት ዘይቤ እንደ ባርሴሎና እንደማይታወስ ገልጿል።

“ ሪያል ማድሪድ በርካታ ዋንጫዎችን አሸንፏል ነገርግን ማንም ሰው ስለ አጨዋወት መንገዳቸው አያስታውስም “ ሲል ፒኬ አስተያየቱን ሰጥቷል።

“ ብዙዎች ሪያል ማድሪድ በታሪክ ምርጡ ቡድን መሆኑን ይገልፃሉ ነገርግን ባርሴሎና በሌላ መንገድ በታሪክ ምርጡ ቡድን ነው ይሄ እኔን ያኮራኛል “ ፒኬ


ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ማክ አሊስተር እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ከተከታያቸው አርሰናል ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አስራ ሶስት ማስፋት ችለዋል።

መሐመድ ሳላህ በአንድ የውድድር አመት በሊጉ በርካታ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ያቀበለ በታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች ለመሆን #አምስት ያህል ቀርተውታል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሊቨርፑል :- 67 ነጥብ
6️⃣ ኒውካስል ዩናይትድ :- 44 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ ሳውዛምፕተን

ሰኞ - ዌስትሀም ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ


74 '

ኖቲንግሃም ፎረስት 0 - 0 አርሰናል

ማንችስተር ዩናይትድ 3 - 2 ኢፕስዊች ታውን
                       
⚽ ሞርሲ ( በራስ ላይ )     ⚽⚽ ፊሎጌኔ
⚽ ዴሊት
⚽ ማጓየር

ቶተንሀም 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ

            ⚽ ሀላንድ

እረፍት | ሊቨርፑል 1 - 0 ኒውካስል ዩናይትድ

⚽ ስቦዝላይ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.