ዩናይትድ ከህክምና ሀላፊው ጋር ሊለያይ ነው !
ማንችስተር ዩናይትድ ከቡድኑ የህክምና አገልግሎት ሀላፊ ዶክተር ጋሪ ኦድሪስኮል ጋር በቀጣይ ለመለያየት ማሰቡ ተገልጿል።
ዶክተር ጋሪ ኦድሪስኮል ባለፈው አመት አስራ ስድስት አመታትን ካሳለፉበት አርሰናል በመልቀቅ ማንችስተር ዩናይትድን መቀላቀላቸው አይዘነጋም።
የ 54ዓመቱ ሀላፊ ጋሪ ኦድሪስኮል አሁን ላይ ከአስራ ስምንት ወራት ቆይታ በኋላ ማንችስተር ዩናይትድን ለመልቀቅ መዘጋጀታቸው ተነግሯል።
በተጨማሪም የዋናው ቡድን የህክምና ባለሙያ የሆኑት ጂም ሞክሶን ከሁለት አመታት ቆይታ በኋላ ክለቡን ሊለቁ መሆኑን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።