ዐርብ የፆም ቀን ስለሆነ ገና ሲያርፍበት ስጋ ይበላል አይበላም የሚለው በአጤ ምኒልክ ዘመን ጭቅጨቅ አስነሳ አሉ። ንጉሠነገሥቱ አሰቡና ስጋ ጭራሽ ወደማይበሉ ዝነኛ አባት መልእክተኛ ሰደዱ።
መልእክቱም “እንዴት እናድርግ? ይጦማል ወይንስ አይጦምም?” የሚል ነበር።
እኚህ አባት መልሱ ግልጽ እንዲሆን ብለው በበዐሉ ዕለት ትንሽዬ የተቀቀለ ስጋ ወደ አፋቸው ወስደው አኘኩ። መልእክተኛውንም መልሰው ላኩት — እንዲህ ብለው: “ጌታየ ተወልዶ የምን ጦም ነው? ፍስሓ ነውንጅ!”
(ከግእዝ መምሕሬ አባ ኅሩይ የሰማሁት ጨዋታ ነው።)
— በድጋሚ የቀረበ። መልካም ገና!
ፎቶዋ: AI ነገር ናት አ? A bit strange