አጼ ቴዎድሮስ ልደታቸው ዛሬ ነው ይላሉ ብዙ ሰዎች። በርግጥ ሦስቱም ዜና መዋዕሎቻቸው አነሳሳቸው፣ ቤተሰባቸውን እና የትውልድ ቦታቸውን እንጂ መች እንደተወለዱ በውል አይነግሩንም። በገደምዳሜ ወደ 1813/14 ገደማ ተወለደ ነው የምንለው። 200+ ዓመታት ማለት ነው። የአንዳንድ ሰው ልጅ ዕድለኛ ነው፡ ከነበረበት ዘመን ሲርቅ ታሪኩ እያማረለት ይሄዳል። ቴዲም እንዲሁ ነው። ከጥፋቱ ይልቅ ሐሳቡ ይመስጠናል አይደለም? ስለዚህም ዛሬ ተወለደ አልተወለደ ብዙ ለውጥ የለዉም ያ እብድ ገና ሲዘመርለት ይኖራል።
በደስታ ተክለወልድ መዝገበ ቃላት ላይ እብዱ ገብረኪዳን የአጼ ቴዎድሮስ የሐሜት ስም የምትል ነገር አለች። (see ደስታ ተክለወልድ፤ ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ገጽ 74)
ቢሆንም፣ ዛሬ እያከበራችሁ ላላችሁ ከአንዱ ዜና መዋዕል በደረስጌ ማርያም እንደነገሠ የተናገረው አዋጅ ተብሎ የተጻፈውን ላሳያችሁ።
«አራሽ እረስ የወንድ መኮንን ሴት ወይዘሮ ባለ ጉልት ባለ እርስት እየአባትህ ሰጥቼአለሁ። ነጋዴም ነግድ በተቀማህበት ቦታ ደንጊያ ደርድረህ ወደኔ ና። ተወኝ ሌባ ተወኝ ወምበዴ ግባ። እቀማለሁ እሰርቃለሁ ብትል ለአካልህ እዘንለት። አይዞህ ድሃ አይዞህ ወታደር ደስ ይበልህ በክርስቶስ ኃይል ወጥቼልአለሁ። የኢያሱ ይብቃ።»
ገጽ 12፣ ስሙ ካልታወቀ ጸሐፊ የተጻፈ ያጤ ቴዎድሮስ ታሪክ፣ ፉሴላ ኤዲት ያደረግው።