የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው መጠለያዎች “የታጠቁ አካላት ሰርገው በመግባት” ጥቃት እንደሚፈጽሙ ኢሰመኮ አስታወቀ
የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚኖሩባቸው ጣቢያዎች “ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግላቸው”፤ የታጠቁ አካላት “ሰርገው በመግባት ጥቃት እንደሚፈጽሙ” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በዚህ ሳቢያ ተፈናቃዮች “አስጊ በሆነ የደህንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ” ኮሚሽኑ ገልጿል።
➡️ ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ይህን ያስታወቀው፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 18፤ 2017 ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ነው።
➡️ ኮሚሽኑ ለሶስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው።
➡️ በስምንት ክልሎች የተፈናቃዮቹን ሰብአዊ መብቶች አያያዝን የተመለከተ ክትትል እና ምርመራ ማድረጉን በሪፖርቱ የገለጸው ኢሰመኮ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታጠቁ ቡድኖች በየጊዜው በሚያደርሱት ማንነትን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ዜጎች እንደሚፈናቀሉ አመልክቷል። በመንግስት እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።
➡️ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያለው የጸጥታ ችግር፤ ዜጎችን እንዲፈናቀሉ ከማድረግ ባሻገር ለተፈናቃዮች ሊደረግ የሚገባውን ሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ “አስቸጋሪ” እንዳደረገው በኮሚሽኑ ሪፖርት ላይ ተገልጿል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14460/
@EthiopiaInsiderNews