የፕሪቶሪያ ግጭት የማቆም ስምምነት ሁለተኛ ዓመት ሲታሰብ፤ ማን ምን አለ?
አቶ ሬድዋን ሁሴን የፌደራል መንግስትን እና አቶ ጌታቸው ረዳ ደግሞ ህወሓትን ወክለው፤ ግጭት የማቆም ስምምነት ተፈራርመው፣ እጅ ለእጅ ከተጨባበጡ፤ ትላንት ቅዳሜ ጥቅምት 23፤ 2017 ድፍን ሁለት ዓመት ሞላቸው። ስምምነቱ ለሁለት ዓመታት በትግራይ ክልል ያጓሩትን ጠመንጃዎች ጸጥ በማሰኘቱ፤ በአቶ ጌታቸው አገላለጽ “ስኬታማ” ነው።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሲቀሰቀስ ለአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ በመሾም ውጊያው እንዲቆም ከፍተኛ ግፊት ስታደርግ የቆየችው አሜሪካ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ትላንት ምሽት ባወጣችው መግለጫ ተመሳሳይ ሀሳብ አንጸባርቃለች። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው ስምምነት ተግባራዊነት ያመጣቸውን “ጠቃሚ መሻሻሎች” አሜሪካ በአዎንታ እንድምትመለከት ገልጸዋል።
ብሊንከን በዚሁ መግለጫቸው “ከምንም በላይ በትግራይ የአፈሙዝ ላንቃ ዝም ብሎ መቆየቱን” አድንቀዋል። በጦርነቱ ምክንያት የተቋረጡ መሰረታዊ አገልግሎቶች እና ሰብአዊ እርዳታ መጀመራቸው፣ የተወሰኑ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዎንታዊ ለውጥነት ጠቅሰዋል።
ታጣቂዎችን ትጥቅ አስፈትቶ በመበተን መልሶ ከማህበረሰቡ ለማዋሃድ የተያዘው ዕቅድ በዚህ ወር ተግባራዊ እንደሚሆን የጠቆሙት ብሊንከን፤ ይህ እርምጃ “ሰላምን ለማጠናከር” “ወሳኝ” እንደሆነ ገልጸዋል። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ ያደረጋቸው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እና የትግበራ ፍኖተ-ካርታ፤ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና እርቅ ለማውረድ መሰረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውንም አስገንዘበዋል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14517/
@EthiopiaInsiderNews