የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “ትኩረት የሚያሻው” “የገቢ እጥረት” እንደገጠመው ገለጸ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘንድሮ በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የሰበሰበው ገቢ፤ በእቅድ ይዞት ከነበረው በ10 ቢሊየን ብር ያነሰ መሆኑን ገለጸ። በዚህ ጊዜ ውስጥ ከውጭ እርዳታ እና ብድር የተገኘው ገቢም፤ ከታቀደው ከግማሽ በታች መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል።
➡️ በከተማይቱ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ ሆነው ሳለ፤ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት የተሰበሰበው ገቢ መቀነሱ “ትኩረት የሚያሻው” መሆኑ ተገልጿል።
➡️ ይህ የተገለጸው፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት አመት አንደኛ የሩብ አመት የስራ አፈጻጸሙን ትላንት ማክሰኞ ህዳር 3፤ 2017 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በገመገመበት ወቅት ነው።
➡️ በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የአስፈጻሚ አካላት የሶስት ወራት የስራ አፈጻጸም፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ አጠር ባለ መልኩ ቀርቧል። በስራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ላይ ከቀረቡ ጉዳዮች መካከል የዕለቱ ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ የነበረው፤ የአዲስ አበባ ከተማ ገቢ ሁኔታ ነው።
➡️ በዘንድሮ በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሰብሰብ ያቀደው ገቢ 54.9 ቢሊየን ብር እንደነበር በትላንቱ የግምገማ መድረክ ላይ ተጠቅሷል። ሆኖም የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ጊዜያት ውስጥ ማሳካት የቻለው የእቅዱን 83.3 በመቶ እንደሆነ አቶ አደም ተናግረዋል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14568/
@EthiopiaInsiderNews