በአዲስ አበባ መርካቶ ገበያ ተደጋጋሚ የእሳት አደጋ ያጋጠመው አካባቢ፤ “በመልሶ ማልማት እንዲለማ” ምክረ ሃሳብ ቀረበ
ከአንድ ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ በትላንትናው ዕለት ለሁለተኛ ጊዜ የእሳት አደጋ ያጋጠመው በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ የሚገኝ አካባቢ፤ “የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ቧሟላ” መልኩ “በመልሶ ማልማት እንዲለማ” ምክረ ሃሳብ ቀረበ። ምክረ ሃሳቡን ያቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ነው።
ትላንት እሁድ ህዳር 8፤ 2017 እኩለ ቀን ገደማ የእሳት አደጋ የደረሰበት የመርካቶ ገበያ ስፍራ፤ በተለምዶ “ድንች ተራ” የሚል ስያሜ ያለው ነው። ስፍራው ከሁለት ሳምንት በፊት በተመሳሳይ አደጋ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ከነበረው “ነባር የገበያ ማዕከል” በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።
የእሁዱ ቃጠሎ የደረሰበት ስፍራ፤ “በነባር የገበያ ማዕከል” ላይ የሚነግዱ ነጋዴዎች ንብረቶቻቸውን የሚያስቀምጡበት መጋዘን እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የእሳት አደጋው “ጌሾ ግቢ” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከሚገኘው መጋዘን በተጨማሪ በአቅራቢያው የሚገኙ መደብሮች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ውድመት አድርሷል።
በትላንቱ የእሳት አደጋ ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሁለት የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
🔴 ለዝርዝሩ:- https://ethiopiainsider.com/2024/14595/
@EthiopiaInsiderNews