ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ “ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ” ተስማሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ፤ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን “ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ” ተስማሙ።
ሁለቱ መሪዎች በአዲስ አበባ እና በሞቃዲሾ “የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ውክልና” እንዲኖር በማድረግ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት “ለማጠናከር” መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ሁለቱ ሀገራት ለአንድ ዓመት ገደማ ሻክሮ የቆየውን ግንኙነታቸውን ለማደስ የተስማሙት፤ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 3፤ 2017 ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው።
አብይ እና ሐሰን ሼክ “በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ መለዋወጣቸውን” የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከውይይቱ በኋላ ያወጣው የጋራ መግለጫ ይጠቁማል።
በመግለጫው መሰረት መሪዎቹ “በሁለቱ ሀገራት ወንድማማች ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ገንቢ ውይይት” አድርገዋል።
የመሪዎቹ ውሳኔ ከአስር ወራት ገደማ በኋላ በሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ወደ ሞቃዲሾ እንዲመለሱ መንገድ ይጠርጋል። ሶማሊያ ተቀማጭነታቸው በሞቃዲሾ የነበረውን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር መሐመድን ያባረረችው በመጋቢት 2016 ዓ.ም. ነው።
🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/14810/
@EthiopiaInsiderNews