ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


ወንድማችን እፎይ የ63+ ሚሊዮን ኦርቶዶክሳዊያን አደራ ነው ይህ ይሰመርበት !!

ጌታ ኢየሱስ ይጠብቀው ጸልዩለት፣ ብዙኀናችን አብሮነታችንን እናሳየው !!

“እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።”
  ማቴዎስ 16፥18
ሐዋርያት 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

¹⁶ ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን አዘወተረ፤ ከፍተውም አዩትና ተገረሙ።
¹⁷ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ ጠቅሶ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣው ተረከላቸውና፦ ይህን ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ አላቸው። ወጥቶም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መንፈሳዊ ፊልም = መቃብር ሰባኪው ክፍል 1 MEKABIR SEBAKIW KEFL 1

ክፍል 2 እንዲለቀቅ ˢʰᵃʳᵉ👍❤️🥰 አይረሳ ።

1.7k 0 19 10 101

ተከታታይ መንፈሳዊ ፊልም ይለቀቅ ❤️

ከ 100 like በዋላ ይለቀቃል 👍❤️
🥰


"እግዚአብሔርን በመንግሥቱ እንዲያስብህ በምትለምንበት መንገድ አንተም በምድር ላይ እርሱን አስብ፥ ልባችሁንም ከፍቅሩ ጋር አጥብቃችሁ ያዙ።" [አቡነ ሺኖዳ ]

አቤቱ ጌታ ሆይ በመንግስት አስበን🤲


ምርኩዜ 🥺
ክፍል ፪
መች በስርአት ተቀምጦ ከእኛ ጋር ያወራል እሱ እንደሆነ ስሙ ቅዱስ ግብሩ እርኩስ ነው እኔ ምለው ግን አንዳንድ ሰው ስሙ አይከብደውም እንዴ አለች ጋሼም ትክዝ ብለው ቀን ጥሎ ቀን ቢጥላት የኛን ድመት አይጥ በላት ነው ነገሩ እናንተ ቅዱሴን የምታውቁት ቢበዛ ሁለት አመት አልያም ደግሞ ከዚያ በታች ነው እሱ ደግሞ ቢያንስ 25 አመት ይሞላዋል ታዲያ የ23 አመቱን ታሪክ ሳታውቁ ዝም ብላችሁ ትፈርዱበታላችሁ አይደል አለ ውይ አባባ ያው የነበረውን ፀባይ ባናውቅም እኖኳኖ በዚች ሁለት አመት በደንብ አይቸዋለሁ ልጁ የማይጠቅም ነው አለች አይ የኔ ልጅ አንቺ ምን አውቀሽ ለምሳሌ አንቺ ስምሽ መቅደስ ነው ግን የምር እንደ ቤተ መቅደስ ንፁህ ነሽ አየሽ አይደል ልጄ ምንም ቢሆን ለመፍረድ አትቸኩይ ለዛ ነው ሊቁ ሰው በማያውቀው ይፈርድብሃል እግዚአብሔር ግን በሚያውቀው ይምርሃል ያለው እና የኔ ልጅ ምን ጊዜም ቢሆን ለመፍረድ አትቸኩይ ቅዱሴ በጣም ባለ ሃብት እናትና አባት ነበሩት አቤት የሚኖሩበት ቤት የሚነዱት መኪና የሚለብሱት ልብስ ብቻ ጉድ ነው ከሱ በኋላ ስላልወለዱ ብቸኛ ልጅ ነበረ ሲንቀሳቀስ እንኳን ብቻውን አልነበረም በአሽከር ተከቦ እንጂ በዚያ ላይ አቤት ቅላቱ የጥርሱ አደራደር ሁሉ ነገሩ ልዑል ነበረ የሚመስለው ያዩት ሴቶች ሁሉ ምነው አሽከሩ ሆኜ ባገለገልኩት ምነው ልብሱን እያጠብኩ ጠረኑን ባሸተትኩት የሚሉለት ጎረምሳ ነበረ ያለውን ለተቸገረ የሚሰጥ የታመመ የሚጠይቅ ደሀ ሀብታም ሳይል ሁሉንም የሚያከብር ለተራበ የሚደርስ ለተጠማ የሚያጠጣ የተራቆተን የሚያለብስ ተወዳጅ ለጋስ ትሁት የተባረከ ልጅ ነበረ ታዲያ የሆነ ቀን ከቤተሰቡ ጋር ዘመድ ለመጠየቅ እየሄደ እያለ ያላሰበው ነገር አጋጠመው ባልታወቀ ቅፅበት በአሸባሪ አካላት ተከበቡ…



ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ


📒ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 🌹

ወር በገባ በ1 የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ወርሐዊ መታሰቢያው ነው፡፡ጸሎቱ በረከቱ ለዘአለሙ ይደርብንና ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ራጉኤል ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡

በጰንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቀራንዮ በሚባል ቦታ በሰቀሉት ጊዜ
ለንጊኖስ የተባለ አንድ ጭፍራ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሣለ ቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፡፡
በዚያም ጊዜ መልአኩ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደሙን ይቀዳ ዘንድ በእጁ የብርሃን ጽዋ ይዞ ቀረበ፡፡

እንደዚሁ መልአኩ ዑራኤል የክርስቶስን ደም በሚቀዳበት ጊዜ ለአይሁድ አልተገለጸላቸውም ነበር ይህም የመላእክት አለቃ ዑራኤል የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ደም በምድር ላይ ከጽንፍ ረጨው፡፡ በዚያን ጊዜም በመላአከ ብርሃናት ራጉኤል እጅ ፀሀይ ጨለመ ጨረቃም ደም መሰለ ከዋክብትም ረገፋ እሱ ራጉኤል መልአክ በፀሐይና በጨረቃ በከዋክብትና በሌሎችም ብርሃናት ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጥቶታልና፡፡

ከብርሃናት አለቃ ከራጉኤል በቀር ፀሐይና ጨረቃን ከዋክብትንም
የሚያዠዛቸዉም የለም፡፡ ፀሐይን በጠፈረ ሰማይ ላይ በቀን ያበራ ዘንድ
አሠለጠነው፡፡ ጨረቃንም ብርሃኑን በሊት ይሰጥ ዘንድ አሠለጠነው፡፡ከዋክብትም እንዲሁ ለሰማይ የፈረጥ ጌት ናቸው፡፡ ዳግመኛም መልአከ ብርሃናት ራጉኤል በከዋክብት ላይ ሰባት አለቆችን ሾመ፡፡

የኒህ የብርሃናት አለቆች የመላእክት ሰማቸው ነቢዮ፤ኢሳይያስ እንደስማቸው ሸረህ መሽተሪህ አጣርድ ዝኁራ፤ዙኃል፤ቀመር ይባላል፡ እነዚህ የከዋክብት አለቆች ታዛዥነታቸው ለመላእክት አለቃ ለራጉኤል ነው፡፡ እሱ በብርሃናት ሁሉ ላይ የሠለጠኀ ነውና፡፡

ልመናው አማላጅነቱ ለሁላችን ይደረግልን፡፡

የጽሑፍ ምንጭ (ድርሳነ ራጉኤል)

ቅዱስ ራጉኤል ህይወት ለጨለመባችሁ ሁሉ ብርሃን ይሆናችሁ፡፡


ዛሬ "የካቲት 30-የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ራስ የተገኘችበት ዕለት ነው፡ በረከት ረድኤቱ ጣእመ ፍቅሩ ይደርብን ምልልስ አይለየን አይለያችሁ።

አጎንብሼ ሄጄ ቀናብዬ መጣሁ
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘሁ

ጌታን ያጠመቁ ክቡራን እጆቹ
ታምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ

አዝ
አልጋዬን አዝዬ በደስታ ዘለልኩኝ
በመጥምቁ ፀበል በጁ ተዳሰስኩኝ
የመራኝን በትር ከጄላይ ጥያለሁ
በሰባኪው ፀሎት በምልጃው ድኛለሁ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አጎንብሼ ሄጄ ቀናብዬ በጣሁ
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን
አገኘሁ ጌታን ያጠመቁ ክቡራ
እጆቹ ታምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ

አዝ ::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::

ለዓለም ያልተቻላት በምነቱ
ለቆኛል አበቃልህ ያሉኝ
እጅግ ተደንቀዋል በለምፅ
የነደድኩት ታደስኩ እንደገና
አዲስ አካል ይዤ ቆምኩኝ ለምስጋና

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

አጎንብሼ ሄጄ ቀናብዬ መጣሁ
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘሁ
ጌታን ያጠመቁ ክቡራን እጆቹ
ታምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ

አዝ :::::::::::::::::::::::::::::::::

ያለፍኩባት ሰፈር በንባ ተሞልቼ
እልልታዬን ሰማች ድኜ ተደስቼ
የንዕማን ቁስል ተራግፉዋልከላዬ
መሞቴን የማይወድ አሰበኝ ጌታዬ

አጎንብሼ ሄጄ ቀናብዬ መጣሁ
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘሁ
ጌታን ያጠመቁ ክብራ እጆቹ
ታምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ

አዝ :::::::::::::::::::::::::::::::::::

ሀባናና ፋርፋን አስንቁዋል ፀበሉ
የዮርዲያኖስ በእምነት ለወረዱ ሁሉ
ዮሐንስ በመንፈስ ሲያጠምቅ
አይቻለሁ በጁ ተፈውሼ ምስክር ሆኛለሁ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

አጎንብሼ ሄጄ ቀናብዬ መጣሁ
በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘሁ
ጌታን ያጠመቁ ክቡራን እጆቹ
ታምር ይሰራሉ ዛሬም ለልጆቹ (2)

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks


✞︎ ዕለተ ሰንበት🌹

🍃ሰንበተ_ክርስትያን🍃

#እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው።ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

📖ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
  ራዕይ 1፥10)


🌹🍃ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

🌹🍃የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የ ዓለማት ሁሉ ገዢ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣቸው አሐዱ ብሎ የጀመረበት ቀን እሑድ ነበር። ፍጥረታትን ፈጥሮ የጨረሰበትና ያረፈበት ቀን ደግሞ ቀዳሚት ሰንበት ነው።

🌹🍃ዳሩ ግን በሐዲስ ኪዳን የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህች ምድር ሲመጣ የማዳኑን ሥራ አጠናቆ ሞትን በሞቱ ደምስሶ የሕይወትን ብስራት ያበሰረበት ለትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በክብር የተነሣው በዕለተ እሑድ ነውና ይህም እለት በሐዲስ ኪዳን ሰንበተ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። እለቱን እንቀድሰው ዘንድም  "የሠንበትን ቀን አክብር" በማለት ትዕዛዝ ከኦሪት ጀምሮ በተሰጠን መሰረት ማክበር የክርስቲያኖቹ ሁሉ ኃላፊነት ነው።

🌹🍃"ሠንበት" እረፍተ ነፍስ የምናገኝባት የገነት አምሳል ነውና እረፍተ ሥጋ እያደረግንበት ሰማያዊቷን ሀገራችንን በማሰብ ቀኑን ልናሳልፈው ይገባል።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን አሜን አሜን 🤲🕊️

🌹🍃_መልካም_ዕለተ _ሰንበት 🍃🌹


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊   [  ሦ ስ ተ ኛ   ሳ ም ን ት    ]   🕊


▷         " ም  ኩ  ራ  ብ "

  [    በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን    ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

[                          🕊                         ]

❝ ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ ፥ ሊያነብም ተነሣ። ❞ 

[ ሉቃ.፬፥፲፮ ]


🕊                       💖                   🕊


የአእላፍት ዝማሬ | Melody Of Myriads dan repost
ኢጃት ለሕፃናት ድጋፍ ለማድረግ ተጨማሪ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረመ።

| ጃንደረባው ሚዲያ | የካቲት 2017 ዓ.ም|

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋራ  ለጋራ ሥራ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ::

በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ስር ካሉት 23 ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ጃን ቂርቆስ ከሰኔ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ እና ከገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 100 ሕፃናት የገንዘብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና፣ የስልጠና እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማም የሕፃናቱ አካላዊ እድገት፣ ጤና፣ የአዕምሮ መጎልበት፣ መንፈሳዊ እድገት አንዲሁም ማኅበራዊ ግንኙነት መዳበር ነው፡፡

በእነዚህ ሁለት አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ ፕሮጀክቱ የሕፃናቱን ሁለንተዊ እድገትን ከማስጠበቅ አኳያ አበረታች ውጤት ስለተገኘበት በያዝነው 2017 ዓ.ም. ደግሞ ተደራሽነቱን በማስፋት ከመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ፣ መንበረ ፓትርያርክ ቅ/ቅ ማርያም ገዳም እና ደብረ ገሊላ አማኑኤል ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ለ 230 ሕፃናት ለሶስት አመት የሚቆይ ድጋፍ ለማድረግ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባው ትውልድ ማህበር እና በሰንበት ትምህርት ቤቶቹ መሀከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።




በአንድም ወቅት በሀገራችን የእህል መታጣት ሆነና ቅድስት እናታችን ዘወትር እንደምታደርገው የኪዳምሕረትን ዝክር ልታደርግ ብላ ዝክሩን የምታደርግበት እህል አጣች፡፡ ደናግል ልጆቿንም ጠርታ ትንሽ ዱቄት እንዲያመጡላት ነግራቸው አመጡላት፡፡ በዚያችም ትንሽ ዱቄት ላይ ጸሎት አድርጋ ከጨረሰች በኋላ ‹ወደ ቦታው መልሱት› አለቻቸው፡፡ በማግስቱም እንስራው ጋኑ ሁሉ በዱቄት ተሞልቶ አግኝተውታል፡፡ ቅድስት እናታችንና ልጆቿም የየካቲት ኪዳነ ምሕረትን በዓል በታላቅ ደስታ አክብረዋል፡፡

መልአኩም እናታችንን ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኋላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ስትደርስ ከቦታዋ ላይ ዓምደ ብርሃን ተጨማሪ ተተክሎ በቀስተ ደማና ተከቦ አይታ ‹‹ይህች ቦታ ምንታምር›› ብላ ጠራቻት፡፡ በ #መድኃኔዓለምም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታለች፡፡ ቦታዋ ዛሬም ድረስ ‹ምንታምር› እየተባለች የምትጠራ ሲሆን ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ የሠራቻት በስሚዛ (በሰንሰል) እንጨት፣ በአይጥ ሐረግ፣ በነጠላ ማገር አድርጋ የግድግዳ ቤተ መቅደስ በአንዲት ቀን ብቻ ሠርታ በታኅሣሥ 16 ቀን በዕለተ እሁድ ቅዳሴ ቤቷን አክብራለች፡፡ በዚህም ጊዜ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤልና ቅዱስ መሲፋይል በክንፋቸው አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው በቦታዋ ላይ ቀላቅለውበታል፡፡ #ጌታችንም ከብርሃን እናቱ ከቅድስት ድንግል #ማርያም ጋር ለፍቅርተ ክርስቶስ ተገልጦላት ቦታዋን ባርኮላት እስከዕለተ ምፅዓትም ድረስ እንደማትፈርስ ቃልኪዳን ገብቶላታል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ወቅት ከባድ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ጫካውን ሁሉ ሲያቃጥል ከቤተክርስያኗ ላይ ግን ለምልክት ያህል ጫፏ ላይ ያለችውን የሰጎን እንቁላል ብቻ አቃጥሎ ቤተ መቅደሷን አልፎ ሄዶ ጫካውን ሁሉ አቃጥሏል፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በአንዲት ቀን ብቻ በተአምራት የሠራቻት ቤተ ክርስቲያኗ ተሠርታ ባለቀች ጊዜ #ጌታችን ለእናታችን ተገልጦላታል፡፡ ጌታችንም በተገለጠላት ጊዜ ቤተ ክርስቲያኗ በአራቱም አቅጣጫ ለ #ጌታችን ሰግዳለች፡፡ ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያኗ በአራቱም አቅጣጫ ሆነው ሲመለከቷት በተቃራኒው አቅጣጫ እየሰገደች ትታያለች፡፡ በምሥራቅ አቅጣጫ ሆነው ቢያዩዋት ወደ ምዕራብ ሰግዳ ትታያለች፤ በምዕራብም ሆነው ቢያዩዋት ወደ ምሥራቅ ሰግዳ ትያለች፡፡ በሰሜን አቅጣጫ ሆነው ቢያዩዋት ወደ ደቡብ ሰግዳ ትታያለች፤ በደቡብም ሆነው ቢያዩዋት ወደ ሰሜን ሰግዳ ትያለች፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በተሰጣት ቃልኪዳን መሠረት በገዳሟም ውስጥ መርዘኛ እባብም ቢሆን ሰውን ወይም እንስሳትን ቢነድፍ መርዙ ምንም አይጎዳም፡፡ እንዲሁም ጌታችን ገዳሟን መናፍቃን ወይም ከሐዲያን እንደማይረግጧት ቃልኪዳን ሰጥቷታል፡፡ ለምሳሌ የጣሊያን ጦር በሀገራችን የተለያዩ ገዳማትን እያጠፋ መነኮሳትን እየገደለ ከፍተኛ ጥፋት ባደረሰበት ወቅት ይህችንም ገዳም ለማጥፋትና መነኮሳቶቹንም ለመግደል መጥቶ ነበር፡፡ መነኮሳቶቹም ይህን ሰምተው ለሰማዕትነት ተዘጋጅተው ጠበቁ ነገር ግን የጦር አዛዡና ሠራዊቱ የገዳሟን ክልል አልፈው መግባት አልቻሉም፣ የገዳሟ ክልል ላይ ሲደርሱ በተአምራት እግራቸው ተሳስሮ መቆም መቀመጥ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ የጦር አዛዡም ‹‹ #ክርስቶስ ከዚች ገዳም አለ›› ብሎ ሃምሳ ጠገራ ብር ሰጥቶ ወደመጣበት ተመልሷል፡፡

#መድኃኔዓለም_ክርስቶስ በዚህች ገዳም ላይ ለቅድስት እናታችን ድንቅ ድንቅ ቃልኪዳን ከሰጣት በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በየካቲት 29 ቀን በታላቅ ክብር ዐርፋለች፡፡ በሥጋዋም ላይ ታላቅ የብርሃን አምድ ተተክሎ የታየ ሲሆን እንደፀሐይም ከጠዋት እስከ ማታ ያበራ ነበር፡፡ በመካነ መቃብሯም ላይ እስከ አርባ ቀን ድረስ ብርሃን ተተክሎ ታይቷል፡፡

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት: በመቂት ወረዳ ጥባ ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ
ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም
የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቷም ይደርብን ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘወርሃ የካቲት 29)


የካቲት 29❤️
#ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (ዕረፍቷ)
✞✞✞


የካቲት ሃያ ዘጠኝ በዚች ቀን ታላቋ ሐዋርያዊት እናታችን የእመ ምኡዝ ቅድስት ፍቅርተ #ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት ዕረፍቷ ነው፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ወይም እመ-ምዑዝ በጎንደር ክፍለ ሀገር በደራ ፎገራ አንበሳሜ በሚባለው ቦታ የአብርሃምና የሣራ ምግባር ካላቸው ከአባቷ ከላባ ከእናቷ ከወንጌላዊት #ጌታችን በተወለደበት ዕለት ታኅሣሥ 29 ቀን በታዘዘ መልአክ አብሳሪነት ተወለደች፡፡ በተወለደችም ጊዜ በእግሯ ቆማ ‹‹በማኅየዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለ #አብ ምስጋና ለ #ወልድ ምስጋና ለ #መንፈስ_ቅዱስም ምስጋና ይገባል›› ብላ አምላኳን አመስግናለች፡፡ ቤተሰቦቿ ያገኙዋት በስዕለት ሲሆን ስመ ክርስትናዋም ማርያም ጸዳለ ተባለ፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ የሚለው የቆብ (የምንኩስና) ስሟ ነው፡፡ ዕድሜዋ ለትምህርት እንደደረሰ #እግዚአብሔር የላከው አንድ ደገኛ መነኩሴ ወደ እርሷ በመሄድ የዳዊትን መዝሙር፣ የብሉያትና የሐዲሳት መጻሕፍትንና የቤተክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ በሚገባ አስተምሯታል፡፡

እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ በነበረችበት ዘመን ዐፄ ሱስንዮስ ‹‹ሁለት ባሕርይ›› የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት የአገራችን ሕዝዝ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ስለተነሣና ከ8ሺህ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖንና ከሌሎችም ቅዱሳንና ቅዱሳት ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነትን ተቀብላ ለሃይማኖቷ መስክር ሆናለች፡፡ ባለቤቷ ዘርዐ ክርስቶስም በሰማዕትነት ዐርፎ ሰባት አክሊላት ወርደውለታል፡፡

ዐፄ ሱስንዮስ ለፖለቲካዊ ጥቅም ብሎ የረከሰች የሮማውያንን ሃይማኖት በአገራችን ላይ እንዳወጀ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖን ካህናትንና ክርስቲያን ልጆቻቸውን አነሳስተው እያስተማሩና እያጠነከሩ እያለ በጦር ተወግተው በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖንም በሰማዕትነት ከማረፋቸው በፊት ግን እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስን፣ ቅድስት አካለ ክርስቶስን፣ ቅድስት እመ ወተትንና ሌሎቹንም ቅዱሳንና ቅዱሳት አነሳስተው ባራ ሄደው ንጉሡን መክረውታል፣ ገሥጸውታል፡፡ ንጉሡ ግን ከፍተኛ ፖሊቲካዊ ጥቅም እንደሚያገኝ ሮማውያን ቃል ገብተውለት ስለነበር ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶች አብዝተው ቢመክሩትም ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይልቁንም ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የሃይማኖቷን ጽናት ስላየ ሥጋዋ እየተቆረሰ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በብረት በትር አጥብቆ ያስገርፋት ጀመር፡፡

በመጨረሻም ምድር እየሰወረቻት ለመግረፍ የማይመቻቸው ቢሆን ከሌሎቹ ሰማዕታት ጋር አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍጹም ጨለማ ሆኖ ምድርም ተነዋወጠች፡፡ ስምንት ሺህ አሥር ቅዱሳንም በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አንገቷን በሰይፍ ቢቆርጧትና በሞት ብታርፍም ነገር ግን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14 ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት አስነሥቶ ወደ ቦታዋ መለሳት፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ከሞት ካስነሣት በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መናኒ ሆና በየገዳሙና በየአድባራቱ እየሔደች ዓለምን ስትዞር ያቀናቻቸው ብዙ ገዳማት አሉ፡፡ ለምሳሌ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ በሆኑት በአባ ጉባ ተመሥርታ በግራኝ ወረራ ጠፍታ የነበረችውን ራማ ኪዳነምሕረት አንድነት ገዳምን አቅንታ የወንድና የሴት ገዳም ብላ ሥርዓት ሠርታለች፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ ሰውን የሚበሉ ፍጡሮች ወደሚኖሩበት አካባቢ ስትደርስ 60 የሚሆኑ አገልጋዮቿን ለመብላት ይዘው ሳር ቅጠል እንዲበሉ በማድረግ ዐይናቸውን በጉጠት በማውጣት 4 ወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጉባቸው፡፡ ሰይጣንንም ያመልኩ ነበርና ከ4 ወራት በኋላም በዓል አድርገው ለመብላት ከእሳት ውስጥ ጨመሯቸው፣ ነገር ግን #ጌታችን በቸርነቱ ጠብቋቸዋልና እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን ምንም አልሆኑም፡፡ ያንጊዜም ሰው በላዎቹ ‹‹እናንተ ሰዎች ምንድን ናችሁ?›› ብለው ጠየቋቸው።

ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስም ክርስቲያን መሆናቸውንና እነርሱ የ
#ሥላሴ ሕንፃ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብታስተምራቸው ‹‹ምን እንበላለን?›› አሏት፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምሕረት ስትነሳ የእህል ዘርን ለአገልጋዮቿ አሰይዛ ስለነበር ከዚያ ስንዴ ወስዳ ዘራችው፡፡ ስንዴውም በአንድ ቀን ብቻ ተዘርቶ በቅሎ፣ ታጭዶ፣ ደርቆ፣ ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡ ቅድስት እናታችንም ቀምሳ ስታቀምሳቸው እንደማር እንደወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርታላቸዋለች፡፡ ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጇ ጽፋ አስቀመጠችላቸው፡፡ እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ምን ያህል የከበረች ‹‹ሐዋሪያዊት›› እንደሆነች ከዚህ ልብ ይሏል፡፡

የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ተገልጣላት በልጇ ምክንያት ስለደረሱባት ሀዘኖች አውርታላታለች፡፡ የፈለገችውንም እንድታደርግበት በእጇ ያለውን #መስቀል ለፍቅርተ ክርስቶስ ሰጥታታለች፡፡ በዚህም #መስቀል እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ ባሕር ከፍላ ደቀ መዛሙርቶቿን አሻግራለች፡፡ የአባታችን የቅዱስ ኤዎስጣቴዎስን ገድል በማንበብና በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እርዳታ ባህሩን በአጽፏ ተሻግራ ወደ ሀገረ ናግራን ሄዳለች፡፡ እንዲሁም በበትረ መስቀሏም እንደ ዘርዐ ቡሩክ ከባሕር ውስጥ የሠጠሙ የደቀ መዛሙርቶቿን መጻሕፍት ምንም ሳይሆኑ ማውጣት ችላለች፡፡ እናታችን በሁሉም ሀገር እየዞረች ቅዱሳት መካናትን ትሳለም ነበር፡፡

በደብረ ዳሞም ሄዳ ‹‹ሴቶች መውጣት አይችሉም›› ቢሏት በሀዘን ስታለቅስ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል በሥውር ወስዶ ከዓምባው ላይ አውጥቶ ከቤተ መቅደሱ አድርሷታል፣ አቡነ አረጋዊም ተገልጸውላት ባርከዋታል፡፡ በዚያም ቅዱሰ ሥጋ ወደሙን በእጃቸው ተቀብላለች፡፡ እናታችን ወደ ኢየሩሳሌምም ሄዳ ቅዱሳት መካናትን እየተሳለመች ለ7 ዓመታት ቆይታለች፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በዓምደ ብርሃን እየመራት ተመልሳ ወደ ሀገራችን መጥታ በድጋሚ ከሱስንዮስ ጋር ተሟግታለች፡፡ ሙታንንም እያስነሳች እንዲመሰክሩለት ብታደርግም እርሱ ግን ከጥፋቱና ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም፡፡ ነገር ግን እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስ የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ መልእክቷንም በንስር አሞራ አድርጋ እየላከች ትመክረው ነበር፡፡


"ቤተክርስቲያን ተስፋህ ናት፤ ቤተክርስቲያን መድኃኒትህ ናት፤ ቤተክርስቲያን የመማፀኛ ከተማህ ናት፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ


ትልቁ ኃጢአት

በሰው ልብ የተተከለው ትልቁ ጠላት ትእቢት Pride ነው።
ትልቁ ኃጢአት ትእቢት።  ትእቢት ራስን ከፍ አደርጎ የማየት፣ ሌላውን የማሳነስ፣ ለእኔ የተሻለው ይገባኛል፣ ሌላውን መናቅ ነው። የሌላው ሕመም የማይገባው፣ የወንድሙ ሳይኾን የራሱ ጥቅምን ብቻ የሚያሰላ ነው። 

ትእቢት ሰው አእምሮውን እያገኘ አዕምሮ እያደገ በመጣ ቁጥር ከመሠረቱ በትንሹ እየበቀለች የምትሄድ ናት። አንዲት ቅንጣት ኾና እንደ ዛፍ ተተክሎ ብዙ ቅርንጫፍ ዘርግቶ ሌሎች አስፈላጊ እጽዋትን እንደሚገድል ዛፍ አይነት ነው። በሰው ሕይወት ውስጥ ትእቢት የተለያየ መገለጫ አለው። 

ይነስም ይብዛም የትእቢት ተክል የሌለበት የለም። እንደ ጥንካሬው እየገደላት እያቀጨጫት ፈጽሞም ያሸነፋትም ይኔራል። አንድ ጊዜ አንዱን ረድእ አበምኔቱ አንተ ትእቢት አለብህ አሉት። እሱም አባቴ በፍጹም ትእቢት የለብኝም አላቸው። በል ተወው  ራስህ ተናገርክ አሉት። ትእቢት የለብኝም ብሎ መናገር በራሱ ትእቢት መኾኑን አስተማሩት። 

የትእቢት መገለጫው አጫፋሪዎቹ ብዙ ናቸው። የተሽቀረቀረ (ፋሽን) አለባበስ፣ ተኳኩሎ ተውቦ መታየት፣ በሌላው በጓደኛው ዘንድ የተሻለ መስሎ መታየት፣ ልጅ በሌላቸው ፊት ልጅ መኖሩ የተባረከ አስመስሎ ማውራት፣ ከሌላው ይልቅ የተማረ መኾኑን ማሳየት፣ የትእቢት መልኬቹ ብዙ ናቸው። ድምጼ አናረልኝ ብሎ ሲዘባነን ማየት፣ ተማርኩ ብሎ አፋን በነጠላ ሸፍኖ ሌላውን የጎሪጥ ማየት፣ ማሽሟጠጥ የመሳሰሉት ኹሉ የትእቢት ቅርንጫፎች ናቸው። 

የማያምኑ የማይጾሙ የማይጸልዩ ሰዎች ስናይ እኛ የተለየ ቅድስና የተሻለ ለእግዚአብሔር ቅርብ የኾንን፣ ከመሰለን ትእቢት ነው። ብዙ ሰው ትእቢት በምን መልክ እንደ በቀለችበት አያውቅም። ስለዚኽም ትእቢቱን እየተንከባደበ ያሳድጋታል። 
አንጀቱ እስኪቆስል ቢጾም፣ ጉልበቱ እስኪላጥ ቢሰግድ፣ እንደ ጊዮርጊስ ብንጋደል፣ ትእቢት እስካለበት ድረስ አይጠቅሙትም። ጽድቅ ያለ ትኅትና አይጠቅምም። 
“ጎልያድ በዳዊት ላይ ታበየ ነገር ግን ለውሻ በሚወነጨፍ ትንሽ ደንጊያ ሞተ። ትሑቱ ዳዊት ግን ለእርሱና ለዘሩ እስከዘለዓለሙ ነገሠ። ትሕትና ከትእግስት ይወለዳልና።” ርቱዓ ሃይማኖት 

ትልቁ ምግባር ትኅትና Humility ነው። “ትኅትና ማለት ክፉ ላደረገብህ በጎ ስታደርግለት ነው።” ይላል።  ዜና አበው 146

ትኅትና ኹሉም ከእኔ ይሻላል ብሎ ማሰብ ነው። ሌላውን ማስቀደም ነው። ትኅትና እስከ መጨረሻው መውረድ ነው። ምንም ሳይኖርኽ ድሃ ነኝ ብትል ትኅትና አይደለም። ምንም ስለሌለኽ ነው። ኖሮኽ እንደሌለኽ ኾኖ ማሰብና መኖር ነው። ክርስቶስ አምላክ ነው። አምላክነቱ ግን በሰዎች መናቅን አላስቀረውም። እመቤታችን የእኛን በደል አልተካፈለችም፣ ሰው አልሰደበች አልተመቀኘች ፣ ገንዘብ አልተበደረች ግን ተሰድባለች፣ ተገፍትራለች። ጸሎቷም 
“የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል” አለች። ሉቃ.1:48

እኛን ያዋረደ ኃጢአት ሳይኔርባት በእግዚአብሔር ፊት ራሷን እንደ ባርያ ዝቅ አደረገች። ባርያ የራሱ ፈቃድ የለውም። የጌታው ነው። እመቤታችን እግዚአብሔር ፈቃድን በምልዓት የፈጸመባት ኪዳኑ ናት። ከፍጥረት በላይ ኾና ራሷን ዝቅ ያደረገች፣ የትኅትና አስተማሪያችን ናት። 
አድርገኽ እንዳላደረግኽ ስታስብ፣ ሰጥተኽ እንዳልሰጠኽ ስታስብ፣ ጠቅመኽ እንዳልጠቀምኽ ስታስብ የትኅትናን መንገድ ጀምረሃል። 

ንዋይ ካሳሁን

4.4k 0 56 11 86

ሠላሜ ነህ ፀትታዮ
ወደቤ ነህ ማረፊያዬ
ሁን ከኔ ጋራ አሁን ከጎኔ
ፍቅር እኮ መድህኔ

https://t.me/Ethiopian_Ortodoks




ምርኩዜ🥺
ክፍል ፩
የሰው ልጅ እንደዚህ ሲንገዳገድ አይቼ አላውቅም አንድ ጊዜ ወደግራ ደግሞ ወደቀኝ ብቻ ምን አለፋችሁ ካሁን ካሁን ወደቀ እያለ ሰው ይመለከታል በሁለት ሊትር ሃይላንድ የተሞላ ድራፍት በቀኝ እጁ ይዟል በግራ እጁ ደግሞ ሲጋራውን ጨብጧል በብብቱ መሃል ደግሞ ጫቱን ይዞ እየተወላገደ ይራመዳል ያገኘውን ሰው ሁሉ እግዚአብሔርን አትከተሉት እንደኔ ያሰቃያችኋል እያለ ይመክራል መንገደኛው ሁሉ ወይ ጊዜ ሰው እንዴት በጠራራ ፀሃይ ይሰክራል እያለ ይመፃደቅበታል ድሮ የሚያውቁት ደግሞ አይ እንደዛ እንዳልተከበርክ በሀይላንድ ፀበሉን በፌስታል እምነቱን በክብሪት ጧፉን እንዳለኮስክ እንዲህ ተበላሽተህ ቀረህ እያሉ ከንፈራቸውን መምጠጥ ከጀመሩለት ሰነባብተዋል የሰፈሩ ህፃናት እንኳን ሳይቀሩ ባዶ እጁን ሲያዩት እንደ አበደ ሰው ነው የሚቆጥሩት ደግነቱ እሱ ባዶውን አይሄድም እንጂ ሁልጊዜ አቋራጭ መንገድ እያለ ወደ ቤቱ የሚገባው ዙሪያ ጥምጥም ሄዶ ነው እንድ ቀን አንድ ሰው ለምን በሚካኤል በኩል አድርገህ በአቋራጭ አትሄድም ሲለው እኔ ሚካኤል በተጠራበት በኩል ማለፍ ስለማልፈልግ ነው እንጂ ዙሪያ ጥምጥም መንገድ ፈልጌ አይደለም ግን እስከለተ ሞቴ በሚካኤል በር አላልፍም አለው ከዚያ ወዲህ ማንም ሰው ጠይቆት አያውቅም ለሰፈሩ አዲስ የሆኑ መጤ ሰዎች አይ ይሄ ሰው በቃ ሁልጊዜ መጠጣት መስከር ነው አይደል የሚያውቀው ሰውስ ቆይ ለምንድን ነው ብር የሚሰጠው አንዳንድ ሰዎች የጠቀሙት እየመሰላቸው በነፍሱ ይጫወቱበታል ወይ ዘመን እያሉ ይማረራሉ ሁልጊዜ ስለሱ መጥፎ ሲወራ የሚያቀጠቅጣቸው አንድ አባት እኔ ምላችሁ ልጆቼ ዛሬ ቅዱስን ያየው ሰው አለ እንዴ አለ አንዷ ቀልጠፍ ብላ ውይ ጋሼ ደግሞ አሁን ቅዱስ እዚህ ይኖራል ብለው ነው ያው እዛው መጠጥ ቤት እየተጋተ ይሆናል እንጂ…

ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ

5.3k 0 48 22 126

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ። [አቡነ ሺኖዳ ]

ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲🌷

4.6k 0 11 13 179

የአእላፍት ዝማሬ | Melody Of Myriads dan repost
አንተ ሰይፍና ጦር ጭሬም ይዘህ ትመጣብኛለህ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው አምላክ ስም በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
1ኛ ሳሙ 17፡45

ዐድዋ - ቅዱስ ጊዮርጊስ ገበዘ ኢትዮጵያ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.