እሷን ብሎ ማርያም🥺
ክፍል ፫
እውነት ለመናገር ገና ሳንደርስ ነበር ግራ የተጋባነው እንዴ ዛሬ በሰላም ነው እንደዚህ ጭር ያለው አለ ሳሚ ሌላ ጊዜ እንኳን የአመት ሆኖ ይቅርና የወር ሲሆን ለራሱ የሚከፍቱት መዝሙር እንኳን ለኦርቶዶክሳውያን ሌላውንም ይመስጣል እና ዛሬ ምን ሆነው ነው ሲል ሱራፌል አይ እኔ የሚመስለኝ ዛሬ ስላረፈድንባቸው ሊያስደነግጡን አስበው ይሆናል አለ በነገራችን ላይ ሳሚና ሱራ አይጥና ድመት በሏቸው አንድ አይነት ሀሳብ እንኳን እያወሩ አይስማሙም የስራ አለቃቸው በሉ በሉ ምንም እንዳታወሩ እናንተ እንደሆናችሁ ከጀመራችሁ አታቆሙም አለችና እየተሳሳቁ በር ላይ ደረሱ በጣም ነበር የደነገጡት እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው አለ ሳሚ ተዘግቶ የማያቀው ግቢ ተጠርቅሟል ሌላ ጊዜ እንኳን የተጠራ ይቅርና ያልተጠራ እንኳን እንዲገባ በሩ ይከፈታል ለየት የሚያደርገው ደግሞ ኦርቶዶክሳውያን ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ሰው ገብቶ በልቶ ጠጥቶ መርቆ የሚወጣበት ቤት ነበረ እንዳውም አንዳንድ ሰዎች ለመግባት ስለሚፈሩ በር ላይ ሁለት ልጆች ቆመው እየለመኑ ያስገባሉ በጣም እቸኩላለሁ ቢል እንኳን በሰሀን ምግብ በሃይላንድ ደግሞ ጠላ ወይም ኬኔቶ አድርገው ሌላ ጊዜ እቃውን በዚህ ስታልፍ ትሰጠናለህ ብለው ነበር አስይዘው የሚልኩት እንዳውም የሰፈሩ ሰውማ ቤተ አብርሃም እያሉ ነው የሚጠሩት ታዲያ ይሄ ቤተሰብ ምን ሆኖ ነው በሩን የዘጋው እ…ነውስ የኑሮ ውድነቱ ከልክሏቸው ነው አለ እየሳቀ ሱራፌል ደግሞ አንተ እንደሆንከ አፍህ ዝም አይልም ሁሉም ነገር የሚሆነው በእርሱ ፈቃድ አይደለ ደግሞ እግዚአብሔር በእጥፍ እንደሚመልስ ረስተህ ነው ወገኛ አለ ወዲያው ሰሎሞን ቁልፉን ከኪሱ አውጥቶ ከፈተው ባዩት ነገር ሁሉም ደርቀው ቀሩ ምንድን ነው እ…
ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ