አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፰
ቆይ ትንሽ አረፍ በል ብሎ ውሃ ሰጠው ምን አይነት ስቃይ ውስጥ ነው የገባሁት ምነው ቅድስት አርሴማ በዚህ ከባድ ጊዜ ከአጠገቤ ተለየሽ ምድር ጨለመችብኝ እ… እናቴ እስኪ ደግፊኝ ህዝቡ ሁሉ የተደገፋት አርሴማ አላሳፈረችውም ብሎ ያውራልኝ እስኪ እናቴ ተአምር ስሪና ዝናሽ በአለም ይሰማ እያለ ማልቀስ የዘወትር ልማዱ አድርጎታል ዛሬ መስከረም 28 ነው ባለቤቱ እስከዛሬ በኩላሊት እጥበት ብትቆይም አሁን ኩላሊት ሊቀየርላት ከሀገር ልትወጣ ነው ልጃቸው ይስሃቅም ለቀዶ ጥገና ከሀገር ሊወጣ ነው በአጠቃላይ ወደ 10ሚሊዮን ብር ይጨርሳል እውነት ለመናገር ብር ኖሮት ሳይሆን ህይወታቸውን ለማትረፍ ሲል ያለውን ሃብት እንዳለ ሽጦ የቀረውን ደግሞ ተበድሮ ነው ይህን ሁሉ መስዋዕትነት እንደ ቀላል ነበረ የቆጠረው ከባዱ ነገር ባለቤቱ የመዳን እድሏ 3%ነው ልጃቸውም በተመሳሳይ 3%ነው ህክምናው ውጤታማ ካልሆነ ደግሞ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱት በሬሳ ሳጥን መሆኑ በጣም አሳስቦታል አባት ሁሉንም በሆዱ ይዞ ሲበሰለሰል ይጨንቃል በጣም ሆድ ብሶት ሲያለቅስ ማየት ደግሞ በጣም ያማል ታዲያ በረራው ከቀኑ10 ሰአት ስለሆነ ወደ 3ሰአት ገደማ ለአሳዳጊው ለቡ አርሴማ አደራ ሊል ጉዞ ጀመረ ከጥቁር አንበሳ እስከ ለቡ አርሴማ ድረስ ማልቀሱን አላቆመም ሁኔታው ያስጨነቃቸው እናት የእኔ ልጅ ምን ሆነህ ነው እንዲህ የምትንሰቀሰቀው አሉት ወዴት ነው የምትሄደውስ አይ እናቴ የማለቅስበት ምክኒያትስ ይቅርቦት የምሄደው ግን ወደ ለቡ አርሴማ ነው ለእናቴ ለሰማዕቷ አደራ የምላት ነገር አለ አላት ይገርማል በዚህ ጊዜ እንዳንተ አይነት ሰው መገኘቱ አሉ ምን ለማለት ፈልገው ነው እማማ አላቸው ደንገጥ ብሎ እኔም ወደ ለቡ አርሴማ ነኝ አብረን ወርደን ቁጭ ብለን አጫውትሃለው ነገሩን…
ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ