አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፱
አይሄዱ አካሄድ እየሄድን ለቡ አርሴማ ደረስንና ወረድን ይገርምሃል የኔ ልጅ ይገርምሃል ከ12አመት በፊት ነበረ ይሄ የሆነው ለብዙ ጊዜ ልጅ አልነበረንም እና ባለቤቴ እና እኔ ሁልጊዜ እንዳማረርን ነበረ ታዲያ ለቅድስት አርሴማ ስለት ተስለን ቆንጆ ሴት ልጅ ወለድን ይገርምሃል አቤት ውበት አቤት ቅላት ሰው ጉድ ነበረ ያለው በወለድኩኝ በሳምንቱ ባለቤቴ ሞተብኝ በጣም አለቀስኩኝ እግዚአብሔርን ሳይቀር ተሳድቤ ነበር እግዚአብሔር ግን በልጄ እና በቅድስት አርሴማ ያፅናናኝ ነበረ አመታት በአመታት ላይ እየተደራረቡ ልጄ 19አመት ሞላት በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝም የምትጠብቅ አስተዋይ ነበረች ከሆነ ጊዜ በኃላ ለረጅም ጊዜ በተከታታይ ይነስራት ጀመረ እናቴ ትጨነቃለች ብላ ስለምታስብ አንድ ቀን እንኳን አልነገረችኝም ነበረ መስከረም 27ቀን ነበረ ልጄ ከእንቅልፏ አልነቃችም ምን ሆነሽ ነው ስላት መልስ አትሰጥም ጠጋ ብዬ ሳይ አንሶላው በደም ተሞልቷል በጣም ደንግጬ ቤቱን በጩኸት አቀለጥኩት ጎረቤት ባንድ ጊዜ ተሰበሰበ ምነው አሰለፍ ምን ሆነሽ ነው ሲሉኝ እኔም ደርቄአለው ፀበሉንም ደፋፍተውብኝ ስነቃ ልጄ ሆስፒታል እንደወሰዷት ነገሩኝ ወዲያውኑ በርሬ ወደ ሆስፒታል ስሄድ ሰው ያለቅሳል ወይኔ ልጄ አንድ ፍሬ ልጄን ምን አደረጉብኝ ብዬ ስጮህ ጋሽ ግርማ ደህና ናት አይዞሽ ተረጋጊ እንጂ የምን ሟርት ነው ብሎ ተቆጣኝ ሲናገሩ በደስታ ያለቅሳሉ እሺ ከዛስ አልኳቸው ወዲያውኑ ሀኪሙ ጠራንና ቢሮ አስገብቶን ሲቀመጥ ልጄ እንዴት ናት አልኩኝ እያለቀስኩ ደህና ናት ነቅታለች ተረጋጉ አለን ይኸውላችሁ በደንብ አድምጡኝ ልጃችሁ የደም ካንሰር አለባት የሚያሳዝነው ደግሞ በጣም ስለዘገየች የመትረፍ እድል የላትም ቢበዛ 1ሳምንት ነው በህይወት የምትቆየው አለን…
ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ