አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፲፩
እናቴ አርሴማ አንቺን የሚሳንሽ እንደሌለ አውቃለሁ ብዙ ጊዜ አስቀይሜሽ አንቺ ግን ሁልጊዜ ይቅር እንዳልሽኝ ነው እባክሽን ሰማዕቷ አንድ ልጄን ፈውሽልኝ እባክሽን ተለመኝኝ ብዬ ከደጇ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ልጄ ትንሽ ቀለል አላት ለሊቱን ሙሉ እያለቀስኩኝ ማህሌቱን እየሰማን አደርን ልጄ አይኗ ተጨፍኖ ሰአታት ተቆጥረዋል አትናገር አትጋገር በጣም ነበረ የጨነቀኝ አይ ቅድስት አርሴማ እንዳታሳፍሪኝ አደራሽን እያልኩኝ ብዙ ለመንኩ የቃል ኪዳኑ ታቦት ምዕመኑን ሊባርክ ከመንበሩ ተነስቶ እልል እየተባለ እያለ ልጄ አይኗን ገለጠች ወዲያውኑ ከአልጋው ላይ ተነስታ መዘመር ጀመረች ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ ቀረ ከእንቅልፏ ጋር አብሮ በሽታው ተኛ በሰማዕቷ አማላጅነት በሽታዋን ትታ ልጄ ነቃች በአልጋ የመጣችው ልጄ በእግሯ ተመለሰች ይገርምሃል የመዳን ተስፋዋ ዜሮ ነበረ እናቴ ግን ፈወሰችልኝ ወዲያውኑ ሆስፒታል ሄደን ስትመረመር ምንም በሽታ የለባትም ተባለ እኔ ያንተ እናት በእልልታ አቀለጥኩት ከዚያ ወደ ቤት እንሂድ ብለን ተነሳን ልጄግን በፍፁም አልሄድም ብላ ወደ ለቡ አርሴማ ሄዳ መነኮሰች በድንገት በጣም የምታምር ሴት ወጣት መነኩሴ ከፊታችን መጣች እማማም እድሜዋ ረጅም ነው አሉ በጣም ነበር የደነገጥኩት እንደዚች አይነት ውብ ምድራዊ ውበትን ንቃ ለክርስቶስ ህይወቷን መስጠቷ አስገረመኝ እኔም ደግሞ የአርሴማ እለት ልክ በ6 በ6የአቅሜን ዘክራለሁ ዛሬ ለካህናቱ ለነገ ምግብ ልሰራ መጥቼ ነው ያገኘኸኝ አሉ እኔም ታሪኬን ዝርግፍግፍ አድርጌ ነገርኳቸው ከዛ እማማ ቤተሰቤን አርሴማ እንድትምርልልኝ ፀልዩልኝ ብዬ አለቀስኩ የእማማ ልጅ እዚህ ይዘሃት ና እናቴ አታሳፍርህም አለችኝ በርሬ ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ሆስፒታል ጉዞ ጀመርኩኝ …
ይቀጥላል
✍ ብርሃኑ ባውቄ