አርሴማን ጥሩልኝ🥺
ክፍል ፲፬
የእውነት አርሴማ ግን ታድንልኝ ይሆን ምናለ የእነሱን በሽታ ወደኔ ተላልፎ ደህና በሆኑልኝ ደግሞ አርሴምዬማ አታሳፍረኝም ከዚያ መኪና ኮንትራት ላናግር ስል ዶክተር አምቡላንስ እንዲያደርሰን ላከልን ዶክተርን እየመረቅን ለቡ አርሴማ ደረስን ፍርሃት ፊቴ ላይ ጎልቶ ይታያል በር ላይ እማማ እና መነኮሳት ተቀበሉን የእማማ ልጅ ቀልጠፍ ብለው መጡና የከበረ የእግዚአብሔር ሰላምታን ከሰጡን በኋላ ይዘውን ወደ ውስጥ አመራን አቤት ትህትና አቤት ቅንነት የሰው ልጅ እንዴት በዚህ ልክ ደግ ይሆናል ከዚያ ወደ መነኮሳት ማረፊያ ሄድን ውስጥ ደግሞ የመነኮሳት ብዛት እንደ አሸዋ ነው ባለቤቴንና ልጄን መሃል አድርገው መነኮሳት ፀሎት ጀመሩ ግሞሹ ተንበርክከው ግማሹ እያለቀሱ እስከ ምሽቱ 4 ሰአት ፀሎት አደረጉልን በመሃል በመሃል ማዕጠንቱ ወንጌል መሳለሙ ብዙ ብዙ ነገር ከዚያ ይዘናቸው ወደ ቤተ መቅደስ አመራን ለሊቱን ሙሉ ሲወረብ ስንዘምር አድረን ስጋ ወደሙ ሲወርድ ልጄ መራመድ ቻለ የተዘገቱ አይኖቹ ተከፈቱ ቤተመቅደሱ በእልልታ ቀለጠ ወዲያውኑ ልጃችን ሮጦ የቅድስት አርሴማን ስዕለ አድህኖ በእንባ ተሞልቶ ተንበርክኮ ሳመ እናት በደስታ አለቀሰች እሷ ግን ተስፋ ያላት አትመስልም በተቃራኒው እየባሰባት ነው ግን በጣም ደስ ብሏታል ልጇ ወንጌል እያሳለመ ፀበል ሲቀዳ ማየት ምኞቷ ነበረ የቃልኪዳኑ ታቦት በእልልታ ታጅቦ ከመንበሩ ሲወጣ ባለቤቴ ከአልጋዋ ወርዳ ተንበርክካ ሰገደች እግዚአብሔር ባለቤቴን ፈወሰልኝ እልልል ሊበጠስ የደረሰውን ህይወቴ አርሴማ ቀጠለችው ልጄ በመዝሙር ተሞልቷል ስመጣ በአልጋ ነበረ ተስፋዬም የተሰበረ በእምነትሽ በፀበልሽ ሰው ሆኜ ቆምኩኝ ደጅሽ የልቡን ለነገረሽ ፈጥኖ ይደርሳል መልስሽ ዘንባባሽ ህይወት ይዘራል የጠራሽ ማን አፍሮ ያውቃል…
ይቀጥላል
✍ብርሃኑ ባውቄ