ጌታዬና አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በዚያ በምኩራብ ስታሰተምር ሳለ ከ18 አመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባትንንና ቀና ብላ ትቆም ዘንድ የማትችለውን ሴት ከድካምሽ ተፈትተሻል ባልካት ጊዜ ቀጥ ብላ እንደቆመች፤ እኔም የኃጢአቴ ብዛት እንደ ሸክም ከብዶኝ ጎብጫለሁና አቤቱ መድኃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሸክሜን አንሳልኝ፤ ቀና ብዬ እንድሄድ እርዳኝ አቤቱ ሆይ እንደ ቸርነትህ
አሜን !
አሜን !