✞︎ ዕለተ ሰንበት🌹
🍃ሰንበተ_ክርስትያን🍃
#እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው።ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።
📖ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
ራዕይ 1፥10)
🌹🍃ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።
🌹🍃የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የ ዓለማት ሁሉ ገዢ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣቸው አሐዱ ብሎ የጀመረበት ቀን እሑድ ነበር። ፍጥረታትን ፈጥሮ የጨረሰበትና ያረፈበት ቀን ደግሞ ቀዳሚት ሰንበት ነው።
🌹🍃ዳሩ ግን በሐዲስ ኪዳን የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህች ምድር ሲመጣ የማዳኑን ሥራ አጠናቆ ሞትን በሞቱ ደምስሶ የሕይወትን ብስራት ያበሰረበት ለትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በክብር የተነሣው በዕለተ እሑድ ነውና ይህም እለት በሐዲስ ኪዳን ሰንበተ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። እለቱን እንቀድሰው ዘንድም "የሠንበትን ቀን አክብር" በማለት ትዕዛዝ ከኦሪት ጀምሮ በተሰጠን መሰረት ማክበር የክርስቲያኖቹ ሁሉ ኃላፊነት ነው።
🌹🍃"ሠንበት" እረፍተ ነፍስ የምናገኝባት የገነት አምሳል ነውና እረፍተ ሥጋ እያደረግንበት ሰማያዊቷን ሀገራችንን በማሰብ ቀኑን ልናሳልፈው ይገባል።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን አሜን አሜን 🤲🕊️
🌹🍃_መልካም_ዕለተ _ሰንበት 🍃🌹