የሕዝብ ትራንስፖርት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት ያለ ታሪፍ ጭማሪ አገልግሎት እንዲሰጥ ተወሰነ!
በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በ4ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ወሰነ።
በውሳኔው መሠረትም ማንኛውም የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶች፣ ሚድ ባስ እና ሚኒ ባሶች ቀን ተመድበው በሚሰሩበት መስመር እና ቀን ላይ በሚከፈለው ሕጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ መመሪያ አስተላልፏል።
የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከ ምሽት 4:00 ሰዓት አገልግሎት እንዲያገኙ መልዕክት ያስተላለፈው ቢሮው፤ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስቧል።
Source:
@Ethiopianbusinessdaily