ኢትዮ ቴሌኮም የእንሰሳት አርቢዎች "የብድር እና የኢንሹራንስ አገልግሎት" በቀላሉ ማግኘት የሚያስችላቸውን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ
በኢትዮጵያ ቀዳሚው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም የድርጅት ደንበኞችን እና ተቋማትን አቅም የሚገነቡ እና የሚያዘምኑ በክላውድ አገልግሎት ላይ የተመሰረቱ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ይፋ አደርጓል።
ከእነዚህም መካከል አንዱ ትኩረት የሚስብ የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ (የእንስሳት ዲጂታል ክትትል) ሲሆን፣ ይህ ሶሉሽን የእንስሳት እርባታን ዘመናዊ በማድረግ እና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሏል።
የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ይህን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ገበሬዎች እና እንስሳት አርቢዎች የከብቶቻቸውን እንቅስቃሴ እና ጤና መከታተል፣ እንዲሁም የብድር እና የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ።
ኢትዮ ቴሌኮም በክላውድ ላይ የተመሰረቱ 7 አዳዲስ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ይፋ ማድረጉ ድርጅቶች የራሳቸውን መሠረተ ልማት ሳይገነቡ የኢትዮ ቴሌኮም ኢንተርኔትን በመጠቀም ሰርቨሮችን፣ የመረጃ ቋቶችን፣ ሶፍትዌሮችን እና ሌሎች ኔትወርኮችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል መባሉን ካፒታል ሰምቷል።
Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily