አሊባባ በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል ሊጀምር ነው
አሊባባ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ አንጋፋው አለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም የሆነው አሊ ባባ እንደገለፀው ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአሊ ኤክስፕረስ የበርካታ አገራትን ገንዘብ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡
ከእነዚህ አገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ ይገኙበታል፡፡ የክፍያ መፈፀሚያ ገንዘቦችን ማስፋፋት ያስፈለገው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች በስፋት ተደራሽ ለመሆን በማሰብ እንደሆነ የጠቀሰው አሊ ባባ በተጨማሪም በአለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለማስቀረት እንደሆነ አስረድቷል፡፡