ኡስታዝ አቡበከርን ላይ እገታ የፈጸሙት ተፈረደባቸው
ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን የተባሉ ግለሰብን በማገት ሊብሬ በመቀየር መኪናቸውን ሊነጥቁ ነበር የተባሉ 5 ተከሳሾች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጥተዋል፡፡
የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ተከሳሾቹ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን መሃመድ የሆነውንና የዋጋ ግምቱ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቪ8 ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ማህደሩን በመለወጥና በሽያጭ በማስተላለፍ ለመውሰድ ሲሉ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡
በዚህም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰው እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዛሬው ዕለት የዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ4 ዓመት ጽኑ አስራት እና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
በተጨማሪም 2ኛ፣ 3ኛ፣4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ከተያዙበት ቀን ጀምሮ እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ2 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡