የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል።
በረራው ወደ 6 አገራት የሚደረግ ሲሆን፤ ሁለቱ ዛሬ ማታ የቀሩት አራት በረራዎች ደግሞ ነገ የሚደረጉ ናቸው።
በረራዎቹ ከካፒፔን እስከ አየር ተቆጣጣሪ እና ቴክኒሻን ድረስ በሴቶች ብቻ የሚደረጉ መሆናቸው ተገልጿል።
ባህርዳር፣ አቴንስ፣ ዴልሂ ፣ዱባይ፣ ሳኦፖሎ እና ዊንድሆክ ከተሞች መዳረሻ ናቸው ተብሏል።
በዓለም ለ114ኛ ጊዜ በአገራችን ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በረራዎቹ መዘጋጀታቸው ነው የተገለፀው።