†
† 🕊 መንፈሳዊው መሰላል 🕊 †
💖
[ ዓ ለ ም ን ስ ለ መ ተ ው ! ]
[ ክፍል ስድስት ]
▬▬▬▬▬▬ ♱ ▬▬▬▬▬▬
የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው ... !
❝ ገና በጅምሩ ከውጊያ ተጋድሎ መዘግየትና በዚህም ምክንያት የመምጣታችንን ምልክት [ማስረጃ] ለገዳዩ መስጠት በጣም የተጠላና አደገኛ ነገር ነው። ጽኑ የሆነ ጅማሮ በርግጥ ኋላ ላይ ደከም ስንል የሚጠቅመን ነው። መጀመሪያ ላይ ብርቱ ፣ በኋላ ግን ዛል የምትል ነፍስ በቀደመ ቅንዓቷ ትውስታ የምትገፋፋ ናት፡፡ በዚህም መንገድ ሁሌም አዳዲስ ክንፎች የሚገኙ ናቸውና፡፡
ነፍስ ራሷን ስትክድና በረከቷን እንዲሁም ትኵሳትን መናፈቅ ስታጣ ፣ ይህ የማጣቷ መንስኤ ምን እንደ ሆነ በጥንቃቄ ትመርምር፡፡ ለዚህ መንስኤው ምንም ሆነ ምን ራሷንም በናፍቆትና በቅንዓት ሁሉ ታስታጥቅ፡፡ የቀደመው ሙቀት ሊመለስ የሚችለው በወጣበት ተመሳሳዩ በር ብቻ ነው፡፡
ከፍርሃት የተነሣ ዓለምን የሚተው ሰው በመዐዛ እንደሚጀምር ዳሩ ግን በጢስ እንደሚጠናቀቅ የሚቀጣጠል ዕጣን ነው፡፡ የሚያገኘውን ዋጋ አስቦ ዓለምን የሚተው ሰው ሁሌም በተመሳሳይ አቅጣጭ እንደ ሚዞር የወፍጮ ድንጋይ ነው፡፡ ነገር ነገር ግን እግዚአብሔርን ከመውደዱ የተነሣ ከዓለም የሚለይ ሰው ገና ከጅምሩ እሳትን አገኘ ፤ ነዳጅ እንደ ተደረገበት እሳትም ፈጥኖ በዝቶ ይቀጣጠላል፡፡ ❞
[ ዮሐንስ ክሊማኮስ [ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው ]
🕊 💖 🕊