ገድለ ቅዱሳን


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


@Gedelat
ለተለያዩ አስተያየት እና ጥቆማ ማድረስ ከፈለጉ በአድራሻችን ቢያደርሱን ይደርሰናል፡፡
በአድራሻችን ✍ @Mnfesawi_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri






†        †        †


❝ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ❞ — [ ማቴዎስ ፫፥፲፫ ]

🕊                      💖                      🕊

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ

Congratulations on the baptism of our Lord and Savior Jesus Christ in peace and health

Baga gooftaa fi fayyisaa keenya Iyyasuus Kiristoos nagaa fi fayyaan cuuphame

እንኳዕ ጥምቀት ጎይታናን መድሓኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ብሰላምን ብጥዕናን ኣብጽሓና።

تهانينا على معمودية ربنا ومخلصنا يسوع المسيح بسلام وصحة
Félicitations pour le baptême de notre Seigneur et Sauveur Jésus-Christ dans la paix et la santé

Herzlichen Glückwunsch zur Taufe unseres Herrn und Erlösers Jesus Christus in Frieden und Gesundheit

[ TMC ]

🕊

[  🕊  ተ ዋ ሕ ዶ   ሰ ማ ያ ዊ ት  🕊  ]

      [  O R T H O D O X Y  !    ]


†                        †                        †
💖                     🕊                     💖






ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩ , ማር.፮፥፲፬ , ሉቃ.፫፥፩ , ዮሐ.፩፥፮]

- " አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ /የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች "

፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ / ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]

አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን::

🕊

[  † ጥር ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት  ]

፩. በዓለ ኤጲፋንያ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
፬. አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
፭. አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
፮. ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት

[   †  ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. ቅድስት ሐና ቡርክት

" ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ :- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::" [ማቴ. ፫፥፲፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


🕊

[  † እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጥምቀት በዓል [ ኤጲፋንያ ] በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  በዓለ ኤጲፋንያ  †    🕊

† "ኤጲፋንያ" የሚለው ቃል ከግሪክ [ጽርዕ] ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ "አስተርእዮ: መገለጥ" ተብሎ ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤጲፋንያ ማለት "የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት" እንደ ማለት ነው::

"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ::
እሳት በላዒ አምላክነ::" እንዲል:: [አርኬ]

አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ ኤጲፋንያ ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ፴፫ [33] ዓመታት ተመላልሷል::

ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር ፲ [10] ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት ፲ [10] ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::

አሥር ሰዓት መሆኑም ርግብ [መንፈስ ቅዱስ] ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::

መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::

ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው::

ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ:: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ" እያልክ አጥምቀኝ አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ : ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ ደነገጠች : ሸሸችም:: [መዝ.፸፮፥፲፮ , ፲፩፥፫] ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውኃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና::

ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::

አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::

ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::


🕊  † ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †  🕊

ቅዱስ ወንጌል ላይ ቅዱስ ሉቃስ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ ሉቃ.፩፥፮ ]

እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ደግሞ ፻ [100] ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫ , ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በኋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ ዓመት ከ፮ ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕፃናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕፃን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕፃን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕፃኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ፫ [፭] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [፯] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕፃኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [፳፫] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ ፴ [ 30 ] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሐ ሰበከ: ለንስሐም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ፮ ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

" እንቢ ጌታየ ! አንተ አጥምቀኝ " አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ ቀናት አሠረው::




❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

             ❤ #ጥር ፲፩ (11) ቀን።

❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ከቀብራቸው በሚወጣው አፈር #በእምነታቸው_ከተለያዩ_በሽታ (ቁስል) ለሚፈውሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሐራ_ድንግል_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                              ✝ ✝ ✝
❤ #አቡነ_ሐራ_ድንግል፡- ጻድቁ ከአባታቸው ከሬማው ካህን ከቅዱስ ዮሐንስ ከእናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ የተወለዱት ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ነው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ጥንት በጌምድር ደብረ ታቦር አውራጃ ደራ ወረዳ ይባል በነበረው አሁን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ነው፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ወላጆቻቸውም አባታችንን ከልጅነታቸው ጀምሮ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ አባታችንም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት በሙሉ ተምረው በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎና አገልግሎት ከኖሩ በኋላ ዓለምን ፍጹም ንቀው መንነው ወደ ሸዋ ተጉዘው ግራርያ ከሚባል አገር ደረሱ፡፡

❤ በዚያም ዘመዶቻቸው ፈልገው ስላገኙዋቸውና ወደ ሀገራቸው ስለመለሷቸው በሌላ ጊዜ ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው አሁን ገዳማቸው ካለበት ጫካ ውስጥ ገቡና ገዳመ ወንያትን መሠረቱ፡፡ በዚያም ፈተናውን ሁሉ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ብርዱን፣ ሐሩሩን፣ ረሃብ፣ ጥማቱን ታግሰው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ ሰይጣንም በፈተና ሊጥላቸው አንድ ጊዜ በተዋበች ቆንጆ ሴት እየተመሰለ አንድ ጊዜ ደግሞ በሞተ ሰው እየተመሰለ እስከ ሰባት ተከታታይ ቀናት ድረስ ቢፈትናቸውም ድል አድርገውታል፡፡ አባታችን ቀን ላይ ጸሎት እያደረጉ እያለ ነብር የሚያባርራት አንዲት ሚዳቋ መጥታ ከቤት ገብታ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግር ስር አረፈች፡፡ ነብሩም ደርሶ ከደጅ እየተቆጣ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አባታችን "እርሷን ገድለህ ትበላ ዘንድ እግዚአብሔር አልሰጠህምና ሂድ" ባሉት ጊዜ ቃላቸውን ሰምቶ ሄደ፡፡ ሚዳቋዋም እዛው አድራ ሲነጋ በሰላም አሰናብተዋታል።

❤ አባታችን መንኵሰው በገዳማቸው ከገቡበት ፈጽመው ሳይወጡ ለ14 ዓመት በተአቅቦ ተቀምጠዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠላት ተነስቶ አካባቢውን በሙሉ በመውረር ሁሉን ሲማርኩ ገዳሟን አይተው ወደ እርሷም ሊገቡ ሲሉ በተአምራት ባሉበት ተይዘው ቆመው በመቅረታቸው ጉዳት ሳይደርሱባት ተመልሰዋል፡፡ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል" የሚለውን የሮማን የረከሰ ሃይማኖት በሀገራችን ላይ አውጆ ብዙዎች ሰማዕትንትን ሲቀበሉ አቡነ ሐራ ድንግል በገዳማቸው ለብዙዎች መጠጊያ ሆነው ሃይማኖታቸውን ሲያስተምሯቸውና ሲያፀኗቸው ነበር፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርበው በድፍረት "አንድ አካልና አንድ ባሕርይ የሆነውን መለኮትና ትስብእትን ለምን ከሁለት ወገን ትከፍለዋለህ?" ብለው ሲገስፁት ፈርቶ አሽከሮቹን "ይህን መነኵሴ ከቤቴ አውጥታችሁ በፍጥነት ወደ ገዳሙ አድርሱልኝ" ብሏቸዋል፡፡

❤ እመቤታችንን እጅግ አድርገው ይወዷት ነበርና ምስጋናዋን ሲያደርሱ ሦስት ክንድ ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም የሁልጊዜ ጠባቂያቸው ነበር፡፡ በ1574 ዓ.ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው ገዳመ ወንያት መንነው ገቡ፡፡ በዚያም ወንጌልን እያስተማሩ፣እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሙት እያስነሱ፣ ድውያንን
እየፈወሱ እግዚአብሔርን ሲያገለገሉ ኖረዋል።

❤ አባታችን ሐራ ድንግል "የማነ ብርሃን" የሚባል ታማኝ አገልጋይ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ጸሎታቸው ይጠብቀው ነበር እንጂ እረኛ አልነበረውም፡፡ አንገቱ ላይ ቃጭል አስረው ወደ ገበሬው አውድማ ይልኩትና አህያውም ቃጭሉን እያጮኸ ወደ አውድማው ሁሉ ሄዶ እየዞረ "ማርያም ባርኪ" በረከት ሰፍረው ይጭኑታል፡፡ አህያውም ከገበሬው ሁሉ የሰበሰበውን እህል ይዞ ወደ አቡነ ሐራ ድንግል ይገባል፡፡ በፈለጉትም ሰዓት ራሱ አውቆ ይመጣላቸው ነበር፡፡ አህያውም አርጅቶ ሲሞት እንደ ሰው አልቅሰውና በአዲስ ጨርቅ ጠቅልለው ቀብረውታል፡፡ አህያቸው የማነ ብርሃን ከተቀበረበት ቦታ ላይ ጸበል ፈልቆ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ የቅዱሳኑ በረከታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን እንደነ በትረ ማርያም፣ ጽጌ ድንግል፣ ወለተጴጥሮስ ያሉ ሌሎችም በርካታ ደጋግ ቅዱሳን ዝናቸውን እየሰሙ ከያሉበት እየሄዱ ይጎበኙዋቸውና በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡

❤ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም  በክብር ካረፉ በኋላ በመካነ መቃብራቸው ላይ ለ40 ቀን ብርሃን ሲወርድ በገሃድ ታይቷል፡፡ አፅማቸውም ከዚያው ከገዳማቸው በክብር አርፎ ይገኛል፡፡ በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበልና የመቃብራቸው አፈር ሕመምተኞችን ከተለያዩ ደውያት ሰውንም እንስሳትንም እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አፈራቸውና ጸበላቸው ለሥጋ ደዌ፣ ለእብጠት፣ለቁስል፣ ለለምፅና ለመሳሰሉት ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ በዓለ ዕረፍታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ዓ.ም ነው፡፡ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።   


https://t.me/Gedelat




❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤

             ❤ #ጥር ፲፩ (11) ቀን።

❤ እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለጌታችን_ለአምላካችን #ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ_ለብርሃነ_ጥምቀቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፋርስ አገር ሰዎች ወገን ከሆነ #ከከበረ_ቅዱስ_እንጣልዮስ በሰማዕትነት ከዐረፈ፣ #ከከበሩ_አዮስጦስና_ከፋይዮስ ዕረፍት፣ ከከበረ ተጋዳይ #ከአባ_ወቅሪስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          
                              
                             ✝ ✝ ✝
❤ በዚች ቀን #የክብር_ባለቤት_ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከአጥማቂው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘንድ_በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም ዕለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው ልዩ የሆነች የሦስትነቱ ምሥጢር ገልጦባታልና አብ ከሰማይ ሁኖ የምወደው በርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት እያለ ሲመሰክር ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቁሞ ሳለ መንፈስ ቅዱስም በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ሲቀመጥ ይህ አጥማቂው ዮሐንስ እንደመሰከረ። እንዳህ ሲል "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከውኃ በወጣ ጊዜ ወዲያኑ ሰማይ ተከፈተ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በጌታችን ራስ ላይ ተቀምጠ ከሰማይም እንዲህ የሚል ቃል መጣ "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ነው እርሱንም ስሙት"።

❤ በዚች ዕለት ጌታችን ራሱን ገልጦአልና ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር ግን በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ እነሆ "የእግዚአብሔር በግ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ" ብሎ መጥምቁ ዮሐንስ እንደገለጠው የከበረ ወንጌል ምስክር ሆነ። "እኔ አላውቅውም ነበር ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ" አለ።

❤ በዚህም በዓል የእግዚአብሔር ልጅ የክርስቶስ የጌትነቱ ክብር ተገልጧል እርሱም የዓለሙን ሁሉ ኃጢአት ለማስወገድ የሚሠዋ የእግዚአብሔር አማናዊ በግ ነው። ስለዚህም ይህ በዓል በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ዘንድ የከበረና ከፍ ከፍ ያለ ሆነ በርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱ በአበረው ውኃ ይነጹበታል የተቀበሉትንም ንጹሕና ጠብቀው ቢኖሩ በውስጡ የኃጢአታቸውን ሥርየት ያገኛሉ።

❤ ስለዚህም ከክፉ ነገር ሁሉ ተጠብቀን የፈጠሪያችንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን የቸርነቱን ብዛት ልመናመሰግን ይገባናል እርሱ ስለ እኛ ሰው ሁኖ ከኃጢአታችን አድኖናልና። ለእርሱም ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ክብር ምስጋና ስግደትም ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥር11 ስንክሳር።

                          ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ባሕርኒ ርእየት ወጐየት። ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ። አድባር አንፈርዐፁ ከመ ሐራጊት። መዝ113፥3-4። የሚነበበው ወንጌል ማቴ3፥13-ፍ.ም።

                           ✝ ✝ ✝
❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ርእዩከ ማያት እግዝኦ። ርእዩከ ማያት ወፈርሁ። ደንገፁ ቀላያተ ማያት ወደምፀ ማያቲሆሙ"። መዝ 76፥16። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 3፥4-8፣ 1ኛ 5፥5-13 እና የሐዋ ሥራ 10፥34-39። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 3፥21-38። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የብርሃነ ጥምቀቱ በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።  


https://t.me/Gedelat






🕊                      💖                      🕊

❝ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን ! ❞

[ ገላ.፭፥፩ ]

🕊                      💖                      🕊

[  ብርሃነ ጥምቀቱን በተቀደሰው ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ! ]

❝ ነገር ግን እላለሁ ፥ በመንፈስ ተመላለሱ ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። ... በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።

የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት ፥ ርኵሰት ፥ መዳራት ፥ ጣዖትን ማምለክ ፥ ምዋርት ፥ ጥል ፥ ክርክር ፥ ቅንዓት ፥ ቁጣ ፥ አድመኛነት ፥ መለያየት ፥ መናፍቅነት ፥ ምቀኝነት ፥ መግደል ፥ ስካር ፥ ዘፋኝነት ፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር ፥ ደስታ ፥ ሰላም ፥ ትዕግሥት ፥ ቸርነት ፥ በጎነት ፥ እምነት ፥ የውሃት ፥ ራስን መግዛት ነው። ❞ [ ገላ.፭፥፲፮-፳፪ ]

🕊                      💖                      🕊

❝ በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ። ❞ [ ፩ጴጥ.፫፥፲፮ ]


🕊                      💖                      🕊






🕊                      💖                      🕊


❝ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ❞ [ ሮሜ.፲፮፥፲፮ ]


[  🕊  ተ ዋ ሕ ዶ   ሰ ማ ያ ዊ ት  🕊  ]

      [  O R T H O D O X Y  !    ]


†                        †                        †
💖                     🕊                     💖






🕊

[    እ ን ኳ ን   አ ደ ረ ሳ ች ሁ ! !   ]

ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ❞ [ ማቴ ፫÷፲፫ ]

🕊                      💖                      🕊

❝ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን። ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ። ... መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች። ❞

[  ቅዱስ ኤፍሬም   ]


❝ ጥምቀትን ለኃጢአት ሥርየት ሰጠን እንዲሁም በዚሁ ጥምቀት ከፍዳ እንድንድንና መንግሥቱን እንድንወርስ አደረገን፡፡ ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]

🕊

ከንግግር ይልቅ ተግባር የገለጸሽ
   ፍኖተ ክርስቶስ ተዋሕዶ አንቺ ነሽ !  ]


🕊                      💖                      🕊

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.