እንኳን ደስ አለን!! ፍኖተ ብርሐን
የስነ አፈታትን ( hermenuetics )ትንታኔ የያዘ መፅሐፍ እንሆ ተብለናል ።
አፕል፣ሙዝ፣አናናስ
እነሆ ተወዳጅ እጅግ ጠቃሚ መፅሐፍ እጃችን ሊገባ የቀናት እድሜ ቀርተውታል ።
በእዚህ አጋጣም ወንጌላዊ ዶር Ev Henok Getachew እንኳን ደስ አለህ!!
በአንድ የስነ አሰባበክ እና አፈታት ስልጠና ላይ የሰማሁትን ምሳሌ በማንሳት ልጀምር
አፕል 🍎 መብላት ብንፈልግ እንዴት ልንበላው እንችላለን ? በቀላሉ በንፁህ ውሃ አጠብ አጠብ አድርገን መግመጥ እንችላለን። አንዴን የቅዱሳት መፅሐፍ ክፍሎች እንዲሁ ናቸው ። በግልፅ ከተፃፈው ውጪ ውስብስብ ትርጉም የላቸውም።
ሙዝ 🍌 እንዴት ልንበላው እንችላለን ። እንደ አፕል አጠብ አጠብ ማድረግ ብቻ አይበቃም ።መላጥ ይጠበቅብናል ።ልፋታችን ብዙ ባይሆንም መላጥ ግን ግዴታ ነው። ምክንያቱም ሳይላጥ የሚበላ ከሆነ ለጤና ልክ ላይሆን ይችላልና ። ከቅዱሳት መፅሐፍትም እንዲሁ የተወሰነ ስራ የሚፈልጉ ክፍሎች አሉ ።አሊያ በቀላሉ ትርጉማቸውን ልናገኝ የምንችላቸው ክፍሎችን በስንፍናችን ምክንያት ሳናገኝ እንቀራለን ።
አናናስ 🍍 ስንመገብ ላጥ ላጥ ማድረግ ብቻ አይበቃም ማጠብ ብቻም አይበቃም።ምክንያቱም ለመብላት የማይመች ብዙ ነገር አለውና ።ስለዚህ ቢላ ወይ ሌላ ማሽን ያስፈልገን ይሆናል። አንዳንድ የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እንዲሁ ናቸው ።በቀላሉ ትርጉማቸውን ማግኘት ከባድ ነው ።ስለዚህ ብዙ ጥናት እና ንባብ ያስፈልጋቸዋል ።ለምን? ያልን እንደሆነ በእኛ እና በፅሁፉ መካከል ያሉ ጋፖችን እነሱን ባለመረዳት የትርጉም መዛባት ውስጥ ልንገባ እንችላለና ።
ለእዚህ ፍቱን መድሐኒቱ እንዴት ቅዱሳት መፅሐፍትን ይጠኑ ?እንዴት ይፈቱ ?የስነ አፈታት መርሐችን እንዴት ይሁን? የሚለውን ማወቅ ነው።
ለእዚህ እጅግ ጠቃሚ መፅሐፍ በወንድማችን ወንጌላዊ ዶር ሄኖክ ጌታቸው ቀርቦልናል። ይህ መፅሐፍ ከአመታት በፊት የታተመ ሲሆን አሁን ዳብሮ ሰፍቶ ብዙ ነገር ተጨምሮበት እንደገና በእጃችን ሊገባ ቀናት ቀርተውታል።
ሁሉም ምዕመን ፣የቃሉ ሰባኪዎች ፣ አስተማሪዎች ፣ የቅዱሳት መፅሐፍትን ትርጉም በጥልቀት ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ይሄ መፅሐፍ ጥቆማዬ ነው ።
በድጋሚ ሄኒ እንኳን ደስ አለህ 🙏🥰🙏