የአክሱም ሙስሊሞች ጭቆና በአክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት (ኡስታዛ)
📍ሐምሌ 1984 አክሱም ላይ ምን ተፈጥሮ ነበር?
📍ይህ ፅሑፍ "አክሱማዊቷ የቁርአን መምህርት" በሚል ነሐሴ 1985 ከታተመው ቢላል መፅሔት የተወሰደ ነው።
"በትግራይ ክልል፤ አክሱም ከተማ ውስጥ የከፍተኛ 2 ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊህ ለዲናችን መጠናከር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በቅርብ የመከታተል እድል አጋጠመኝና አርአያነታቸውን ላወሳችሁ ወደድኩ።
ወ/ሮ ሸምሲያ ሸህ ሷሊሕ ከሰላሳ አምስት በላይ ህፃናትን ቁርአን በማስቀራት ታላቅ ተግባር የፈፀሙ የሙስሊሞች መኩሪያ ናቸው። እኚህ ደርባባ ወ/ሮ ሲናገሩ ረጋ ያሉና ገፅታው የበራ ነው። ቁርአን ማስቀራት የመጀመራቸው ጉዳይ ከአባታቸው ጋር የተያያዘ ነው። አባታቸው ሸህ ሷሊህ ቁርአን ያስቀሩ ነበር። እርሳቸው ሲሞቱ የቁርአን ትምህርቱ ተቋረጠ። በዚህን ጊዜ በአካባቢው የሚገኙ ሙስሊሞች ወ/ሮ ሸምሲያን "ለምን አንቺ አታቀሪም? እርሳቸው ሳሉም ብዙውን ጊዜ የምታቀሪና ቁርአኑን በሉህ (አነስተኛ ጣውላ) የምከትቢው አንቺው አልነበርሽምን?" ብለው ወተወቷቸው። ወ/ሮ ሸምሲያም "እናንተ ከተቀበላችሁኝ ደስታዬ ነው" በማለት ልጆቹን ሰብስበው ማቅራት ጀመሩ። ቁርአንን ለማስቀራት የሚከለክል ምክንያት /ዑዝር/ ሲገጥማቸው አንጋፋ ተማሪዎቸቸው በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን እንዲያቀሩ ውክልና እንደሚሰጡ አውግተውኛል-በጣፋጭ አንደበት።
ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን ማስቀራት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ [1980ዎቹ] ድረስ አያሌ ተፈታታኝ ችግሮች ገጥሟቸዋል። ከእነዚህም ውስጥ ጎላ ብለው የተፈታተኗቸውን እንዲህ ሲሉ አወጉኝ። "እንደምታውቀው እኛ የአክሱም ሙስሊሞች የግላችን ቤት አልነበረንም። ሀብታምም ይሁን ድሃ የአክሱም ሙስሊም የሚኖረው በኪራይ ቤት ነበር። ቤት ለመስራት አይፈቀድልንምና! ይህ በኋይለስላሴ ጊዜ የነበረ ጭቆና ሲሆን ደርግ መጣና ሙስሊም አክሱም ውስጥ ቤት እንዳይሰራ የሚከለክለውን እገዳ አንስቶ መሬት ሰጠን። ታዲያ በክራይ ቤት እኖር በነበረበት ጊዜ ልጆችን ሰብስቤ ቁርአን ሳቀራ አከራዮቼ "ቤታችንን የልጆች መሰብሰቢያ አድርገሽ ልታፈርሺብን ነው..." በማለት በማቅራቴን እንዳቆም ይጠይቁኝ ነበር። እኔ ግን ጥያቄያቸውን አልቀበል ብዬ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። እነርሱም ከቤታቸው ያስወጡኛል። እንደገና ሌላ ቤት ተከራይቼ ማቅራቴን እቀጥላለሁ። ትንሽ ቆይተው እነዚህም ይቃወሙኛል። እንዲህ እያልኩኝ የግሌን ቤት እስካገኝ ድረስ ከሀያ ቤቶች ተባርሬያለሁ።
ይህን ካወጉኝ በኋላ የትዝታ ቅኝታቸውን ወደቅርቡ ዘመን መለሱት። እናም እንዲህ አሉኝ። "እንደምታስታውሰው ሐምሌ 1984 በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የ"ክተት" አይነት ዘመቻ ተጠንስሶ ነበር። በዚያን ጊዜ እኔ ከሌሎች ሙስሊም ጎረቤቶቼ በበለጠ ተሳድጃለሁኝ። የዚህም ምክንያት ቁርአን የማቀራ ስለሆንኩኝ ነው። አልሐምዱሊላሂ ጎረቤቶቼ ጋር ተደብቄም ቢሆን ነፍሴን አትርፌአለሁ። ሆኖም ግን እኛን ለማጥቃት የተነሱት ሰዎች እቤቴ ድረስ ገብተው የማቀራበትን ቁርአን ቀደድው ሉሑን ሰባብረው ቤቴ ላይ ያለ እቃ አንድ እንኳ ሳይቀር ሰባብረውብኛል።
በውይይታችን መሀል "እስላም የሴቶችን የመማር እድል ይነፍጋል" የሚለው የአላዋቂዎች አሉባልታ ድንገት ትውስ አለኝና ነገሩን አጠገቤ ካሉት እንስት መምህር ጋር አስተያይቼው በውስጤ ሳቅሁኝ። እናም "ሴት አስተማሪ /ቁርአን አቅሪ/ በመሆንዎ የደረሰብዎት ችግር አለን" ብዬ ለወ/ሮ ሸምሲያ ጠየቅኋቸው።
"በእውነቱ ሴት አቅሪ በመሆኔ አንድም የደረሰብኝ ችግር የለም፤ እንዲያውም ብዙዎች ይደሰቱብኛል። ባለቤቴም ለዲኔ በማደርገው እንቅስቃሴ ፍፁም ደስተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አጥብቀው ያበረታቱኛል። እንዳውም አንዳንድ ጊዜ ህመም ቢጤ ጫን ሲለኝና ድካም ሲበረታብኝ ህፃናቱ እንዳይጉላሉና እንዳልጨነቅ ብለው እርሳቸው ያስቀራሉ።" አሉኝ።
ወ/ሮ ሸምሲያ ቁርአን በማቅራት ላሳለፏቸው ረዥም አመታት በእጅጉ እንደሚያስደስታቸው አውግተውኛል። "አየህ" አሉኝ በጣፋጭ አንደበታቸው "ሌሊቱን ታምሜ አድሬ ጠዋት ተማሪዎቼ ሲመጡ በሽታዬ ይለቀኛል። መቼም እነሱን በማቅራቴ የሚሰማኝን ደስታ እኔን አንድ አላህ ብቻ ነን የምናውቀው። "
እኒህ የተባረኩ ወ/ሮ በአሁኑ ጊዜ [1985] ከሁለት መቶ ህፃናት በላይ በግቢያቸው ውስጥ ያቀራሉ። ልጆቹን ሰብስበው የሚያቀሩት በግቢያቸው ውስጥ በሚገኝ ጥላ ቦታ ላይ ነው። ይህ ቦታ ጠንከር ያለ ፀሐይ እንዳያጠቃቸው የሚከላከልላቸው ቢሆንም ቅሉ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ለማቅራት አመቺ አይደለም። ወ/ሮ ሸምሲያ እንደነገሩኝ ከሆነ አላህ በጭድ የተሸፈነ ጣሪያ ቢጤ ያለው ቤት እንኳ የመስራት አቅም ቢሰጣቸው በእጅጉ ይደሰቱ ነበር። ትልቁ ችግርና ጭንቀታቸውም ከፀሐይና ከዝናብ የሚከላከል ጎጆ ቢጤ መቀለሱና ህፃናቱም ተመቻችተው የሚቀመጡበት ወንበር አለማግኝታቸው ነው። ወ/ሮ ሸምሲያ ለዲናችን ከሚያበረክቱት ታላቅ አስተዋጽኦ አኳያ ያለባቸውን ችግር ከጎናቸው ሆኖ መቅረፉ የአህለል ኸይሮችን ትኩረት የሚሻ ይመስለኛል። የሚመለከተውም ክፍል ችላ ሊላቸው አይገባም ባይ ነኝ። "
_
በነገራችን ላይ ኡስታዛ አላህ ረጅም እድሜ ሰጥቷቸው አሁኑም በአክሱም ከተማ በህይወት አሉ። ከአንድ አመት በፊት Nur Quran Bank Islamic Association / ኑር የቁርኣን ባንክ ኢስላማዊ ማህበር ወደ አክሱም ተጉዘው በነበሩ ጊዜ በኔ ጥቆማ ቤታቸው ድረስ ሄደው እንደዘየሯቸው እና በነብዩ ሙሐመድ ሰላዋት ሲያወርዱ ቀርጿቻዋል።